የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

Send-a-Cow-Reportertenders-1
1
2

Overview

 • Category : Fuel & Related
 • Phone Number : 0913077065
 • Source : Reporter
 • Posted Date : 07/28/2021
 • Closing Date : 08/11/2021
 • E-mail : [email protected]

Description

የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ        የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያየማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን በኩታበር ወረዳ በመተግበር ላይ ለሚገኘው ለኮቪድ19 ምላሽ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ መስሪያ ሞልዶችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን በዘርፉ የተሰማራችሁና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

 • ተጫራቾች የዘመኑን (2013 ዓም) ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድና ከሚመለከተው የመንግስት አካል የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው ፤የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ቁጥር ያላቸው ፣የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን ይጠብቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዳቸውን ከታች በተገለጸው አድራሻ እስከ ማክሰኞ 27 ቀን 2013 ዓም ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ዝርዝር ስራውን በሚመለከት የጨረታ ሰነዱን ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች መውሰድ ይኖርባቸዋል
 • ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ በትክክል መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ከጨረታው መዝጊያ ቀን በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናት በድርጅቱ ጨረታ ኮሚቴ አማካኝነት ተከፍቶ አሸናፊው በአድራሻው የሚገለጽለት ይሆናል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡

አድራሻ

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከመገናኛ ወደ ሲ ኤም ሲ መንገድ ሲቪል ሰርቪስ አለፍ ብሎ ከጊብሰን ት/ቤት ፊት ለፊት ጎልጎታ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 011-647-72-33/34/35፣ ወይም ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ኩታበር ፕሮጀክት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0334480463/65 እንዲሁም 0913077065 መጠየቅ ይቻላል፡፡