የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጨርቃጨርቅና አልባሳት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ፋብሪካዎች የሥራ ዋስትና መርሀ ግብር ለመደገፍ የወጣ ማስታወቂያ

Ministry-of-Laibor-Logo-ReporterTenders

Overview

 • Category : Legal Consultancy
 • Posted Date : 04/18/2021
 • E-mail : contact@savingjobs.org
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/18/2021

Description

በጨርቃጨርቅና አልባሳት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ፋብሪካዎች የሥራ ዋስትና መርሀ ግብር ለመደገፍ የወጣ ማስታወቂያ

 የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአለም የስራ ድርጅት እና ከጀርመን መንግሥት የፌዴራል የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚ/ር (BMZ) ጋር በመተባበር በሃገር በቀል ጨርቃጨርቅና አልባሳት ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኛች የሥራ ዋስትናን የሚያስጠብቅ መርሀግብር አዘጋጅቷል፡፡

የመርሀ ግብሩ ዋና አላማ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ተመዝግበው በሚገኙ ሃገር በቀል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችን ደመወዝ ወጪ በመሸፈን ፋብሪካዎቹን ለማበረታታትና ሠራተኞቹም በሥራ ላይ እንዲቆዩ ያለመ መርሀግብር ሲሆን በተለይም በኮቪድ 19 ምክንያት ከሚፈጠር ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎችና ተጋላጭነቶችን በመቀነስ ፋብሪካዎቹ የሰው ኃይላቸውን በሥራ ላይ እንዲያቆዩ በማድረግ በቀጣይም ዘላቂና ችግርን የሚቋቋም የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

ይህ መርሀ ግብር በዓለም አቀፍ የማህበራዊ ዋስትና ደረጃዎች ከተቀመጡ መርሆዎች ጋር ተቀናጀቶ የተቀረጸ ሲሆን፣ በተለይም መብት ላይ ተመስርቶ የማህበራዊ ጥበቃ፣ ቀጣይነት ያለው ማህበራዊ ምክክር ከሥራ ዕድል ፈጠራ ፖሊሲዎች ጋር እንዲጣጣም ተደርጐ የሚተገበር ነው፡፡

ለሥራ ዋስትና መርሀ ግብሩ ብቁ ለመሆን የሚችሉት ፋብሪካዎች የሚመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ ፋብሪካዎች ይሆናሉ ፡፡ ለመርሀግብሩ ብቁ የሚሆኑት አመልካቾች ፣

 1. በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራት የጸና የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
 2. በግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና ዐቅድ የተመዘገቡና የ2012 በጀት አመት የጡረታ መዋጮ የከፈሉ፣
 3. ከሌሎች የልማት አጋራት፣ የመንግስትና የግል ድርጅቶች በተመሳሳይ የደመወዝ ድጋፍን ተጠቃሚ ያልሆኑ፣
 4. በ2012 የበጀት አመት ጠቅላላ ሽያጭ ወይም የሥራ ትዕዛዝ መቀነስ ወይም የትርፍ ገቢያቸው 40

በመቶ ስለመቀነሱ በተረጋገጠ ኦዲተር የሂሳብ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣

ለመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ መሆን የሚሹና ብቁ የሆኑ ፋብሪካዎች ለዚሁ አላማ ሲባል በተዘጋጀው https://saving-jobs.org/am/ ድህረ ገጽ ውስጥ መመዘገብ ይችላሉ፡፡

ይህንን መርሀግብር በዋናነት የሚያስተባበረው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን ለዚሁ ተግባር ተፈጻሚነት በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና የሚመለከታቸው የመንግስት የማህበራዊ ዋስትና እና የአሠሪና ሰራተኛ ማህበራት ተወካዮች ያሉበት አብይ ኮሚቴና ዝርዝር የቴክኒክ ስራዎችን የሚያስተባብር የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

ስለሆነም በመርሀ ግብሩ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው በጨርቃ ጨርቅ አልባሳት ዘርፍ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች በተዘጋጀው መርሀግብር ተጠቃሚ ለመሆን የተመለከተውን ድህረ ገጽ በመጎብኘትና የተዘጋጀውን የምዝገባ ቅጽ በመሙላት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ድረስ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያውን ዙር ማጣርያ ያለፉ ፋብሪካዎች ስም ዝርዝር ከላይ በተመለከተው ድህረ ገጽ የሚገለጽ ሲሆን አመልካቾች ለተከታይ ምዘና የሚጠየቁትን ማስረጃዎች በድህረ ገጹ በመጠቀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ለዚህ ተግባር የተቋቋመው የሦስትዮሽ አብይ ኮሚቴ ማመልከቻዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማጣራት አመልካች ፋብሪካዎች ድጋፉን ለማግኘት ብቁ ስለመሆናቸው ወይም ስላለመሆናቸው ከላይ በተመለከተው ድህረ ገጽ ውሳኔውን ያሳውቃል፡፡

ማሳሰቢያ:-                 

 •  ለዚህ መርሀ ግብር ተጠቃሚነት ማመልከት የሚገባቸው ፋብሪካዎች ሲሆኑ ሠራተኞች በግል ማመልከት አይችሉም፡፡
 •  በድህረ ገጽ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተሟልቶ የተላከ ማመልከቻ ብቻ ለምዝገባ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
 •  ለዝርዝር የማመልከቻ አቀራረብ ድህረ ገጹና መጎብኘት ወይም በ (contact@savingjobs.org) ኢሜይል መላክ ይቻላል ፡፡