የሰንጋተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት  ኃ/የተ/የሕ/ሥ/ማህበር ከ 2010 እስከ 2013 የ አራት አመትት ሂሳብ ለማስመርመር/ኦዲት ለማስደረግ/ ይፈልጋል

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 06/08/2021
 • Phone Number : 0911569869
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/08/2021

Description

የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

የሰንጋተራ የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት  ኃ/የተ/የሕ/ሥ/ማህበር ከ 2010 እስከ 2013 የ አራት አመት ሂሳብ ለማስመርመር/ኦዲት ለማስደረግ/ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ስራ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

 1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN-No) ያላቸው ።
 2. ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (A.A.B.E) የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያላቸው ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ።
 3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
 4. ጨረታው በ8ኛው ቀን እሮብ ሰኔ 9 ከቀኑ በ10፡00 ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ በ10፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ።
 5. የጨረታው ውጤት የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለፅ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም ።
 6. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል ።
 7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ተወዳዳሪዎችን ለአገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋ እና ስራውን ሠርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ የሚገልፅ ፕሮፖዛል በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንድታመለክቱ እናሳስባለን ።

አድራሻ፡- ሜክሲኮ ሰንጋትራ 40/60 የጋራ መኖሪያ አፓርትምንት ብሎክ 5 በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ ወይም በስልክ ቁጥር +251-5-574861 +251 911569869 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

የሰንጋተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት  ኃ/የተ/የሕ/ሥ/ማህበር