የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር በቀድሞ ሳሪስ ገበያ አካባቢ ከሪየስ ኢንጅነሪንግ አ/ማ አጠገብ የሚገኝ በርከት ያሉ የንግድ ዘርፎች የሚገኙበትን የገበያ ማዕከል ባለንብረት ሲሆን የ2013 ዓ.ም. በጀት ዓመት ሒሳቡን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Accounting Related
  • Posted Date : 09/09/2021
  • Phone Number : 0114422121
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/21/2021

Description

የሒሳብ ምርመራ ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ

የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር በቀድሞ ሳሪስ ገበያ አካባቢ ከሪየስ ኢንጅነሪንግ አ/ማ አጠገብ የሚገኝ በርከት ያሉ የንግድ ዘርፎች የሚገኙበትን የገበያ ማዕከል ባለንብረት ሲሆን የ2013 ዓ.ም. በጀት ዓመት ሒሳቡን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1ኛ. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ

2ኛ. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት

3ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት

4ኛ. ተመሳሳይ በሆኑ ድርጅቶች የሒሳብ ምርመራ ሥራ ልምድ ያለው መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ

5ኛ. የበጀት ዓመቱን የሒሳብ መዛግብት በአ/ማህበሩ ጽ/ቤት በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡

6ኛ. የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7ኛ. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የጨረታው ሰነድ ይከፈታል፡፡

አክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ሳሪስ ከሪየስ ኢንጅነሪንግ አክሲዮን ማህበር አጠገብ የሚገኘው የገበያ ማዕከል ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 442 2121 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡

የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር