የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል አገልግሎት የሚዉሉ የአይሲቲ ዕቃዎችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Computer Purchase
 • Posted Date : 01/23/2023
 • Phone Number : 0118132198
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/03/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል አገልግሎት የሚዉሉ የአይሲቲ ዕቃዎችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች:-

 1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ  የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
 2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሣብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ የዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር  በመሙላትና የጨረታ ማስከበሪያ በማካተት በአገልግሎት ዋና መ/ቤቱ የግዢ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2%  ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት –Refugees and Returnees Service  በሚል የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም  የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋt 04፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፤

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ምስኪ ህንፃ ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ

አዲስ አበባ

ለተጨማሪ ማብራሪያ፤

በስልክ ቁጥር  011 813 21 98  ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

አዲስ አበባ