የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት የጎርፍ ውሃ ማሰባሰቢያ የድንጋይ ኩሬ ግንባታ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
Overview
- Category : Other Construction
- Posted Date : 04/18/2021
- Phone Number : 0468830266
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/27/2021
Description
የጎርፍ ውሃ ማሰባሰቢያ የድንጋይ ኩሬ ግንባታ ሥራ
ጨረታ ማስታወቂያ-በድጋሜ የወጣ
(Rock Pond Construction Labor Work Service-Rebiding )
የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት በዘላቂ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት በቡኢ-ዙሪያ ቀበሌ የጎርፍ ውሃ ማሰባሰቢያ የድንጋይ ኩሬ ግንባታ(Rock Pond Construction) አስፈላጊ የግንባታ ቁሳቁሶችን አሰሪው ድርጅት እራሱ በግዢ አቅርቦ በጥራትና በአግባቡ መስራት የሚችሉ በዘርፉ የደረጃ-8 እና ከዚያ በላይ የውሃ ሥራዎች ግንባታ(WWC) ወይም ጠቅላላ የግንባታ ሥራ(GC) ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተቋራጮች/ማህበራት ለጉልበት/ሙያ ሥራ አገልግሎት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- በዘርፉየታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ::
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጨማሪእሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ ወይም ሲ.ፒ.ኦ የአጠቃላይ የጨረታ ዋጋውን 1%ማስያዝ የሚችሉ::
- አሸናፊውተጫራች የተፈለገውን የኩሬ ግንባታ ሥራ አጠናቆ በተፈለገው ጊዜ ውስጥ እንዲያስረክብ ይጠበቅበታል% ካጠናቀቀ በኃላ በውል መሰረት ሕጋዊ ደረሰኝ በማቅረብ ክፍያውን ይረከባል፡፡ እንዲሁም ተገቢው የመንግስት ታክስ ተቀናሽ ይሆናል::
- የውሃ ቁፋሮ/ግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ መልካም የስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ወይም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾችይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣበት መደበኛ የስራ ቀን ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ የጨረታ ሰነዶችን ቡኢ ከተማ ከሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በብር100/አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት መደበኛ የስራ ቀን ጀምሮ በ7/ሰባተኛ/ ክፍት የስራ ቀናት ውስጥ በ7ኛው ቀን እስከ 8፡00ሰዓት ድረስ በኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ አሽገው በድርጅቱ ግቢ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ጨረታዉየሚከፈተዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ማስታወቂያ በወጣበት በ7ኛው መደበኛ የስራ ቀን ከቀኑ8፡30ሰዓት በድርጅቱ ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱየተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ሶዶ ቡኢ የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት%ቡኢ ከተማ ‘ሶዶ ወረዳ’ጉራጌ ዞን’
ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ-ምዕራብ አቅጣጫ 103ኪ.ሜ በአለምገና-ቡታጅራ/ሆሳና ዋናው አስፋልት መንገድ
የስልክ ቁጥር፡ 046-8830266 ወይም 0468830265 ወይም 0468830350 ወይም 0468830023