የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት የጣሊያን እና/ወይም የህንድ ስሪት የሆነ በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ሰመርሲብል የውሃ ፓምፕ(Solar power operating submersible water pump) አቅራቢ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Sodo-Buee-Child-and-family-development-charity-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Solar & Photovoltaic
 • Posted Date : 06/05/2021
 • Phone Number : 0468830266
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/14/2021

Description

ሰመርሲብል የውሃ ፓምፕ አቅርቦት/ሽያጭ

 ጨረታ ማስታወቂያ

የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት የጣሊያን እና/ወይም የህንድ ስሪት የሆነ በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ሰመርሲብል የውሃ ፓምፕ(Solar power operating submersible water pump) አቅራቢ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡  ስለዚህ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉና በሽያጭ ማቅረብ የምትችሉ በጨረታው መሳተፍ  ትችላላችሁ፡፡

የሰመርሲብል ፓምፑ-ስፔሲፊኬሽን

ውሃ-የመሳብና የመግፋት አቅም ርቀት(Discharge head) 250ሜትር እና የውሃው አቅም(Discharge or Yield)፡ በሰከንድ 4.1ሊትር የሆነ’ለ6ኢንች ኬዚንግ  የሚገጠም በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ:: 

 1. ተጫራች አቅራቢዎች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ::
 2. ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ /15%ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ:: ተጫራቾች ለውድድር ያቀረባችሁት ዋጋ 15%ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በዋጋ ማቅረቢያችሁ ቅጽ ላይ በጽሁፍ መግለጽ ይጠበቅባችኋል%በጽሁፉ ካልተገለጸ ግን የቀረበው ዋጋ 15%ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 1. አሸናፊው ሻጭ/አቅራቢ የተፈለገውን ዕቃ/ቁሳቁስ በተፈለገው ጊዜ ውስጥ በአሸነፈበት ዋጋ ማረከብ ይጠበቅበታል% ሕጋዊ ደረሰኝ በማቅረብ ክፍያውን ይረከባል’ተገቢው የመንግስት ታክስም ተቀናሽ ይሆናል ::
 1. ተጫራቹ ይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ የተገለጸውን ዕቃ የምትሸጡበትን የአንዱን ዋጋ በድርጅታችሁ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በ7/ሰባት/ ተከታታይ ክፍት የስራ ቀናት ውስጥ  በታሸገ ኢንቨሎፕ ቡኢ ከተማ በሚገኘው የድርጅታችን ቅጥር ግቢ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 1. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ የዕቃውንና ቁሳቁስ መሸጫ ተለይቶ መሆን አለበት% የኢንስታሌሽን/ዝርጋታ አገልግሎት እና ትራንስፖርት ዋጋም ለየራሱ ተለይቶ ይቅረብ፡፡
 1. ተጫራቾች በፀሃይ ሀይል የሚሰራ ሰመርሲብል የውሃ ፓምፕ ካላችሁም መሸጫ/አቅርቦት ዋጋውን በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ ሀይል ከሚሰራው ሰመርሲብል የውሃ ፓምፕ ለይታችሁ እንድትገልጹ፡፡  
 1. የጨረታዉ ሳጥን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው/የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ እንዲሁም ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ 8፡30ሰዓት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 2. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፡-ሶዶ ቡኢ የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት%ቡኢ ከተማ ‘ሶዶ ወረዳ’ጉራጌ ዞን’ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ-ምዕራብ አቅጣጫ 103ኪ.ሜ በአለምገና-ቡታጅራ/ሆሳና ዋናው አስፋልት መንገድ፡፡

             የስልክ ቁጥር፡  046-8830266  ወይም  0468830265  ወይም  0468830350 ወይም  0468830023         

Send me an email when this category has been updated