የቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ አጠቃላይ የኦዲት ምርመራ ሥራ ለማከናወን ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ የኦዲት ተቋማትን ይጋብዛል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 07/03/2021
 • Phone Number : 0115157819
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/09/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ፤

የቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ አጠቃላይ የኦዲት ምርመራ ሥራ ለማከናወን ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ የኦዲት ተቋማትን ይጋብዛል፡፡

 1. መርማሪ አካላት ግብዣ፤

የሚጋበዙት የቅድስት ልደታ ጤናና ቢዝነስ ኮሌጅ በ2010፣ 2011፣ 2012ና 2013 ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት መርምሮ ሪፖርት ለማቅረብ ነው፡፡

 1. ምርመራውን የሚያዘው አካል ፍላጎት፣

ምርመራው እንዲከናወን የሚያዘው አካል የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የኮሌጁ ሥራ አመራር ቦርድ ነው፡፡ ፍላጎቱም በራሱ መንገድ መርምሮ የደረሰባቸውና ማስረጃ የያዘባቸው የአሠራር ግድፈቶችና ብልሽቶች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩ፣ የችግሮች ጥልቀትና የጉዳት መጠን እንዲመረምር ነው፡፡

 1. የሚከናወኑ የምርመራ ዓይነቶች፣

ኮሌጁ ዝርዝርና አጠቃላይ ምርመራ እንዲከናወን የሚሻ ሲሆን፣

 • የፋይናንስ ምርመራ (Financial Audit)
 • የአፈፃፀም ምርመራ (Performance Audit)
 • የሕጋዊነት ምርመራ (Compliance Audit) በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡
 1. ምርመራው የሚመሠረትባቸው ሰነዶች፣

ለምርመራ ሥራው በርከት ያሉ ሰነዶች ሥራ ላይ የሚውሉ ሆኖ በዋናነት ግን፡-

 •  በቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጋጀውና በ1998 ዓ.ም. የተሻሻለው የኮሌጁ ማቋቋሚያ ደንብ፣
 •  የኮሌጁ መምሪያ ሕግ (legislation)
 •  የፋይናንስ ማኑዋል፣
 •  የንብረት አስተዳደር ማኑዋል፣
 •  የመደበኛና ትርፍ ሰዓት የሠራተኛ አስተዳደር ማኑዋል፣
 •  የግዥ ማኑዋል፣
 •  የገቢና የወጪ ደረሰኞችን፣
 • የባንክ ስቴትመንቶችን፣
 • ቃለ-ጉባኤዎችን፣
 • ልዩ ልዩ ሪፖርቶችንና የመሳሰሉትን መሠረት ያደርጋል፡፡
 1. ከተመርማሪው ተቋም አካላት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት፣

መርማሪ ድርጅቱ የምርመራ ሥራውን ከመጀመር አስቀድሞ ስምምነት መፈጸምና ከሥራ አመራር ቦርዱ አቅጣጫ መቀበል ይኖርበታል፡፡ የኮሌጁ ማኔጅመንት የሚጠየቁ ሰነዶችን በማቅረብ፣ ጥያቄዎችን በመመለስና ለምርመራ ሥራው የሚመች ሁኔታን በመፍጠር የምርመራ ሂደቱን ያግዛል፡፡

መርማሪው ድርጅቱ በየደረጃው ለሚገጥሙት ችግሮች መፍትሄ ለመስጠትና የምርመራ ሥራውን ለመከታተል ቦርዱ ኮሚቴ የሚሰይም ይሆናል፡፡ የመርማሪ ድርጅቱ መሠረታዊ ግንኙነትም ከዚህ ከሚቋቋመው ኮሚቴ ጋር ይሆናል፡፡

 1. የመርማሪ ድርጅቱ ገለልተኛነት፣

ርማሪ ድርጅቱ በማንም ተፅእኖ ሥር አይደለም፡፡ ገለልተኛነቱን ጠብቆ ይሠራል፡፡ ከማንኛውም አካል በሥራው ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነገር በገጠመው ጊዜ የገጠመውን ችግር ቦርዱ ላቋቋመው ኮሚቴ ያቀርባል፡፡ ከኮሚቴው ጋር መግባባት ባይኖር ችግሩን ለሥራ አመራር ቦርዱ አቅርቦ መፍትሄ ማግኘት ይችላል፡፡

 1. የምርመራ ጊዜ፣

መርማሪ ድርጅቱ የተጠቀሱትን ዓመታት ተቋማዊ እንቅስቃሴ በአራት ወራት ውስጥ በሦስቱ ዘርፎች መርምሮ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡

 1. ሌሎች
 • ኦዲት ለማድረግ የተሰጠውን ሕጋዊ የሞያ ፈቃድ ማቅረብ፤
 • ከዚህ በፊት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የኦዲት ሥራ የሠራ፤ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
 • በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬትና ሌሎች መረጃዎች ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 1. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 2. ከላይ በተራ ቁጥር 03 ከተዘረዘሩት የምርመራ አይነቶች በአንዱ ወይንም በሁሉም መወዳደር ይቻላል፡፡ ለዚህም በየትኛው የምርመራ አይነት እንደሚወዳደሩ ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ በግልጽ ማመላከት አለበት፡፡በሁሉንም ዘርፎች ለመወዳደር የማይችል ተጫራች የምርመራ ጊዜው በተራ ቁጥር 7 በሶስቱም የኦዲት ዘርፎች የተገለጸውን የኦዲት ማጠናቀቂያ ጊዜ መሰረት ተደርጎ የሚሰላ ይሆናል፡፡ 
 3. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይችላሉ፡፡

                    ****የቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ****

አድራሻከባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፊት ቅድስት ልደታ ህንጻ ቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 ለበለጠ መረጃ በ0911 19 59 99 ወይም 011 515 7819 መደወል ይችላሉ፡፡

Send me an email when this category has been updated