የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

Announcement
BUNNA-INTERNATIONAL-BANK-S.C-S-2

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/29/2022
 • Phone Number : 0111580880
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/04/2022

Description

 የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366፣367፣ 370፣ 371፣ 372፣ 394 እና 400 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 9.4 እና በመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 6.3 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ ባንኩ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡ 3,314,741,000 ብር፣

የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡ AR/AA/3/0003357/2006፣

የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት የሚገኝበት ቦታ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር፣ አዲስ፣

የ13ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፣
 2. በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ ማፅደቅ፤
 3. እ.ኤ.አ የ2021/22 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 4. እ.ኤ.አ የ2021/22 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 5. እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን አበል መወሰን፤
 6. እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2021/22 በጀት ዓመት ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 7. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 8. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡

6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣
 2. የባንኩን የመመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻያ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 3. የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

 1. በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመቅረብ የውክልና ቅጽ በመሙላት፣ የውክልና ቅፁን ዋናውንና አንድ ቅጂ እና የራሳቸውንም ሆነ የወካዮቻቸውን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜግነት የሚያሳይ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/ መንጃፈቃድ ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው በመምጣት በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡
 2. በተጨማሪም የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ ጉባዔ ወይም ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ ውክልና ዋናውንና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
 3. የባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻያ ሰነድ ከባንኩ ድረ-ገጽ ላይ በማውረድ ማግኘት ይቻላል፡፡
 4. ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0111 580880/262822/262810 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ቡና ባንክ አ.ማ

የባለራዕዮች ባንክ