የቡና ባንክ አ.ማ የ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

Announcement
Bunna-International-Bank-Logo-reportertenders-5

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/24/2021
 • Phone Number : 0111580880
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/13/2021

Description

የቡና ባንክ አ.ማ

የ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ከዚህ ቀደም በወጡ ማስታወቂያዎች መግለጻችን ይታወሳል። ነገር ግን የስብሰባ ቦታና ቀን ለውጥ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት ስብሰባው ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ጦርሃይሎች በሚገኘው ጎልፍ ክለብ የሚካሄድ ሲሆን የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣
 2. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ መወሰን፣
 3. የባንኩን የመመስረቻና የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል፣
 4. የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ የሚሉት ናቸው፡፡

የ12ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፣
 2. በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ መርምሮ ማፅደቅ፤
 3. እ.ኤ.አ የ2020/21 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 4. እ.ኤ.አ የ2020/21 የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 5. እ.ኤ.አ የ2021/22 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን አበል መወሰን፤
 6. እ.ኤ.አ. የ2021/22 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 7. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ መወሰን፤
 8. ባንኩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ፣
 9. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ የሚሉት ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

 1. በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ባለው የመንግስት አካል ሕጋዊ ውክልና መስጠት ከሚችል የተሰጠ በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመቅረብ የውክልና ፎርም (ቅጽ) በመሙላት፤ ሌላ ሰው በመወከል የውክልና ሰነዱን ወይም ቅፁን ዋናውንና አንድ ቅጂ ይዘው በመምጣት በጉባዔው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡
 2. ባለአክስዮኖችም ሆኑ ተወካዮች ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውንም ሆነ የተወካዮቻቸውን ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን መያዝ አለባቸው፡፡
 3. ባንኩ የባለአክሲዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት የተንቀሳቃሽ ስልክ የሚልክ ሲሆን፤ ይህንኑ ቁጥር በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትመጡ በአፅንዖት እንጠይቃለን፡፡
 4. ከላይ በተ.ቁ 2 ላይ የተገለጸውን የወካዩን ዜግነት የሚያረጋግጥ ሕጋዊና የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ኮፒ ይዘው የማይመጡ ተወካዮች በጉባዔው ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ ጉባዔ ወይም በውል አዋዋይ ፊት የተሰጠ ውክልና ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
 5. የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የሚካሄደው የኮሮና ወረርሽኝ ባለበት ወቅት በመሆኑ ወረርሽኙን ለመከላከል ሲባል ባለአክሲዮኖች በጉባዔው በውክልና እንዲሳተፉ ይበረታታሉ፡፡የጉባኤው ተሳታፊዎች የኮረና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥንቃቄዎችን አድርገው እንዲሳተፉ እናሳስባለን፡፡
 6. ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0111 580880/262822/262810 በመደወል ማግኘት ይችላሉ

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ቡና ባንክ አ.ማ

የባለራዕዮች ባንክ

ማረሚያ

በተ.ቁ 6 የተመለከተው አጀንዳ በስህተት አለመካተቱ ስለታወቀ እንዲካተት ተደርጎ መታረሙን ለባለአክሲዮኖችና ለባለድርሻ አካላት ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን፡፡