የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 04/03/2021
 • Phone Number : 0111243459
 • Source : Reporter, Addis Fortune
 • Closing Date : 04/15/2021

Description

በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር– ብ/ፓ/ዋ/ጽ-01/2013

 

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 • ሎት፡- 1 የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች
 • ሎት፡- 2 የጽዳት ዕቃዎች
 • ሎት፡- 3 የመኪና ዲኮር ዕቃዎች
 • ሎት፡- 5 አይሲቲ ዕቃዎች
 • ሎት፡- 6 ፎቶ ኮፒ ማሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1, በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

 • የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
 • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
 • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
 • የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ያላቸው
 • በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
 • ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል

2. ተጫራቾችየጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 ብር በመክፈል አራት ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 1-23  በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾችለዕያንዳንዱ ሎት00 አምስት ሺህ ብር ለአይሲቲ ዕቃዎች እና ኮፒ ማሽን ለእያንዳንዳቸው 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ብቻ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታውን ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወድያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡

4. ተፈላጊውንየጥራት ደረጃ ያልጠበቀ ዕቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል፡፡

5. ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾችየሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ ቫትን አካቶ ያለውን ድምር በመጨመር ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት እና ኦሪጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒውን ለብቻ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾችለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ከ3 ቀናት በፊት ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ኮምፒተርና የፎቶኮፒ ማሽን ሎት ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን በተለያየ ፖስታ በመለየት ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም

9. ጨረታውበ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

10. የጨረታሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡

11. አንዱ ድርጅት በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡

12. መ/ቤቱጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13.ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-24 34 59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት

 

Send me an email when this category has been updated