የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ጽ/ቤቱ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ አይነት መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Prosperity-party-Logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 01/23/2023
 • Phone Number : 111243461
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/10/2023

Description

ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- ብ/ፓ/ዋ/ጽ-01/2015

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ጽ/ቤቱ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ አይነት መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ አካል ተሸከርካሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ አራት ኪሎ ፓርላማ ፊለፊት እና ሃያ ሁለት አክሱም ሆቴል ጀርባ በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ፡፡

 • ማንኛውም ተጫራች ከአንድ በላይ ተሸከርካሪዎችን ለመግዛት መጫረት ይችላል፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከጽ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-02 መውሰድ ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙበትን የአንዱን ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋው በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ በብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 • ተጫራቹ በአሃዝ እና በፊደል በሰጠው ዋጋ ልዩነት ካለ ጽ/ቤቱ በፊደል የተፃፈውን ዋጋ በመውሰድ ጨረታውን ያወዳድራል፡፡
 • ማንኛውም ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ በመሙላት እና ኦሪጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
 • ጨረታው ይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ቀናት አየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ሲሆን በጨረታ አከፋፈት ስነ ስርአቱ ላይ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
 • ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ በ2 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመፈጸም በአንድ ሳምንት ጊዜ ማንሳት አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ያስያዙት ሲፒኦ ለጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ሁለተኛ ለወጣው ተጫራች ይተላለፋል፡፡
 1. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
 2. አንዱ ድርጅት በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 3. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-24 34 59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት