የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የተጠቆሙ እጩ የቦርድ አባላት ስም ማስታወቂያ

Berhan-Insurance-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/14/2022

Description

የተጠቆሙ እጩ የቦርድ አባላት ስም ማስታወቂያ

የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ በሥራ ላይ ያለው የዳይሬክተሮች ቦርድ የስራ ዘመን የሚያበቃው በ2015 ዓ.ም በመሆኑ በምትካቸው አዲስ የቦርድ አባላት ለመምረጥ እንዲቻል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 10ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ መመረጡ ይታወሳል፡፡ ኮሚቴው ባወጣው የጋዜጣ ማስታወቂያ እና በግል ለእያንዳንዱ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በተላከ ደብዳቤ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች እጩ የቦርድ የዳይሬክተሮችን የመጀመሪያ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ የሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ጥቆማ እንዲያቀረብ ባደረገው ጥሪ መሠረት ከአባላት ጥቆማ የተቀበለ ሲሆን የሚከተሉት ባለአክሲዮኖች በ11ኛው የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላት ሆነው ለምርጫ የሚቀርቡ መሆናቸውን ያስታውቃል፡፡ በመሆኑም በቀረቡት እጩዎች ላይ ሃሳብ፣ አስተያየት ወይም ተቃውሞ ካለ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲያቀርቡ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የእጩ ቦርድ አባላት ስም ዝርዝር

በሁሉም ባለአክሲዮኖች የተጠቆሙ                ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ የተጠቆሙ

 1. ወ/ሮ ዘውዴ በላቸው መሸሻ አቶ አዲሱ ደምሴ ባዬ
 2. ወ/ሮ መልክርስት ኃይሉ ወርቅአገኘሁ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከበደ
 3. ወ/ሮ ይመናሹ ካሳሁን መኮንን                             አቶ ግሩም ፀጋዬ ካሳ
 4. ዶ/ር ሳለሁ አንተነህ ተማረ                                            አቶ በየነ አለሙ ወ/ማርያም
 5. አቶ ጃለታ ወርዶፋ ጉራራ                                               ዶ/ር ታዬ ብርሃኑ ካሳ
 6. አቶ ተስፋ ታደሰ ፊዳ                                       ጆሽዋ ሁለገብ አ.ማ (ተወካይ) አቶ ኃይሌ ነሩ ሙራረ
 7. አቶ ሲቢሉ ቦጃ ገላልቻ     ተጠባባቂዎች
 8. አቶ ፈለቀ ጥበበ ወ/ሰማያት                                           አቶ መሳይ እምሩ ሀይሉ
 9. አቶ አለሙ ገበየሁ ወንድምተገኝ አማረ ፈለቀ ጋሻሁን
 10. አቶ ደስታ በካሎ ሳፓ
 11. አቶ ታደሰ ሀጠያ ሀጌ
 12. አቶ ተመስገን ኃ/ሚካኤል ፍርቱስ

ተጠባባቂዎች

 1. ቲ.ኬ ኢንተርናሽናል (ተወካይ) ኢ/ር ፈረደ ይትባረክ
 2. ኤደን ቢዝነስ አ.ማ

የዳይሬክረቶች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ