የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ የተለያዩ መያዣቸው የተጎዱ ዘይቶችና ቅባቶችን፣ ባዶ ጀሪካኖችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

yetebaberut-Beherawi-logo-2

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 11/27/2021
 • Phone Number : 0118787565
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/09/2021

Description

    የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ

Yetebaberut Beherawi Petroleum s.c

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን የተለያዩ መያዣቸው የተጎዱ ዘይቶችና ቅባቶችን፣ ባዶ ጀሪካኖችን እና ቁርጥራጭ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ዝርዝሩ የጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ መረዳት ይችላሉ፡፡ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-

 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው፣
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
 4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ/ ብር በመክፈል በዋናው መ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
 5. ጨረታው ከህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፣
 6. ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
 7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ 15 በመቶ በተጨማሪነት ይከፍላሉ፣
 8. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር ቃሊቲ ቶታል ወረድ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 • በጥቅል ወይም በተናጠል የዋጋ ውድድር በማከናወን አሸናፊውን መለየት የኩባንያው መብት ነው፡፡
 • ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- 22 ማዞሪያ በውሃልማት መ/ቤት ወረድ ብሎ ከስሪዴይስ /3 Days/ ሆቴል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0118-78-75-65 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Send me an email when this category has been updated