የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ የጥበቃ አገልግሎት እንዲሁም ለዋና መሥሪያ ቤቱ የጽዳት/ ተላላኪ፣ የሾፌር እና እንግዳ ተቀባይ የሚሰጡ ልምድ ያላቸው ሙያተኞችን የሚያቀርቡ ድርጅቶችን ከዚህ በታች ለተወዳዳሪዎች በቀረበው ዝርዝር መግለጫ መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Cleaning & Janitorial Service
- Posted Date : 09/24/2021
- Phone Number : 0116638577
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/08/2021
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ 22 ማዞሪያ ከውሃ ልማት ገባ ብሎ ለሚገኘው ዋና መ/ቤት፣ ቃሊቲ ለሚገኘው ንብረት ክፍል እና አየር ጤና ለሚገኘው የነዳጅ ማደያ ፕሮጀክት የጥበቃ አገልግሎት እንዲሁም ለዋና መሥሪያ ቤቱ የጽዳት/ ተላላኪ፣ የሾፌር እና እንግዳ ተቀባይ የሚሰጡ ልምድ ያላቸው ሙያተኞችን የሚያቀርቡ ድርጅቶችን ከዚህ በታች ለተወዳዳሪዎች በቀረበው ዝርዝር መግለጫ መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ዝርዝር መግለጫ
- ተወዳዳሪዎች ኩባንያው በሚፈልጋቸው በሁሉም የሥራ መደቦች መወዳደር የሚችሉና በጥበቃ አገልግሎት፣ በጽዳት/ ተላላኪ፣ በሾፌር እና እንግዳ ተቀባይ ሙያተኞችን ለማቅረብ በግልጽ የሚገልጽ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፣
- ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን ከመርሃ-ግብር ጋር በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፣
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ከታች በተገለጸው አድራሻ እስከ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባዋል፣
- የጨረታ ሰነዱ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤቱ 2ተኛ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የስራ መደብ ለአንድ ሠራተኛ የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት በፊትና በኋላ ያለውን የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ በውሃ ልማት ወረድ ብሎ ከ 3-ዴይስ /3 days/ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ /ሚኪሊላንድ መንገድ/
ለበለጠ መረጃ ፡- ‘ 0116-63-85-77/80/, 0118-95-94-95 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡