የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. የተጠቆሙ እጩ የቦርድ አባላት ስም ማስታወቂያ

Nyala-Insurance-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/07/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/07/2022

Description

የተጠቆሙ እጩ የቦርድ አባላት ስም ማስታወቂያ

የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. በስራ ላይ ያለው የዳይሬክተሮች ቦርድ የስራ ዘመን የሚያበቃው በ2015 ዓ.ም. በመሆኑ በምትካቸው አዲስ የቦርድ አባላት ለመምረጥ እንዲቻል የኢትዮጽያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ኅዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው 27ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጡ ይታወሳል፡፡ ኮሚቴው ባወጣው የጋዜጣ ማስታወቂያ እና በግል ለእያንዳንዱ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በተላከ ደብዳቤ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች እጩ የቦርድ ዳይሬክተሮችን የመጀመሪያው የጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ጥቆማ እንዲያቀርቡ ባደረገው ጥሪ መሰረት ከአባላት ጥቆማ የተቀበለ ሲሆን የሚከተሉት ባለአክሲዮኖች በ28ኛው የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላት ሆነው ለምርጫ የሚቀርቡ መሆናቸውን ያስታውቃል፡፡ በመሆኑም በቀረቡት እጩዎች ላይ ሃሳብ፣ አስተያየት ወይም ተቃውሞ ካለ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲያቀርቡ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የእጩ ቦርድ አባላት ስም ዝርዝር

በሁሉም ባለ አክሲዮኖች የተጠቆሙ

 1. ዶ/ር ሳራ ሱሩር መሐመድ
 2. ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማ
 3. ዳሽን ባንክ አ.ማ.
 4. ወ/ሮ ምንትዋብ አበበ አውራሪስ
 5. ካቤ ኃ/የተ/የግ/ማ
 6. አቶ አብደላ ሁሴን አሊ አላሙዲ
 7. ወ/ሮ ማርታ ዱጉማ ሁንዴ
 8. አቶ ሪያድ ዳማጅ ጋዜም
 9. ናሽናል ሞተርስ ኮርፖሬሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
 10. አቶ ዮናስ ዱጉማ ሁንዴ
 11. አቶ መርዱፍ ሳሊም ባዝሃም
 12. አቶ ሱሩር መሐመድ ዘይን

ተጽእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች የተጠቆሙ

 1. አቶ ሰለሞን በዳኔ ጉራሮ
 2. አቶ ታደሰ ጥላሁን መንግስቴ
 3. አቶ ሁሴን አህመድ ሀሰን
 4. አቶ ጣሂር መሐመድ ቲጃን
 5. አቶ ብሩክ ዱጉማ ሁንዴ
 6. ወ/ት ቤዛ ዱጉማ ሁንዴ

      ተጠባባቂዎች

ወ/ሮ ቅድስት ዱጉማ ሁንዴ

አቶ መስፍን ረጋሳ ባልቻ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ