የናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ እና 25ኛ አስቸኳይ ጉባዔ

Nile-Insurance

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/02/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/03/2022

Description

የስብሰባ ጥሪ

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 366፣ 393፣394 እና በኩባንያዉ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 3(1) መሠረት የናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ እና 25ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በቦታው ተገኝተው እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 1. መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ(28 የባለአክሲዮኖች ጉባኤ)

1.1 የጉባዔውን ጽ/ቤት ማቋቋም፣

1.2 የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣

1.3 እ.ኤ.አ በ2021/2022 የተከናወኑ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣

1.4 እ.ኤ.አ የ2021/2022 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማድመጥ፣

1.5 እ.ኤ.አ የ2021/2022 የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርትን ማድመጥ፣

1.6 በተራ ቀጥር 1.4 እና 1.5 በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.7 በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈልን በሚመለከት የዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው  የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.8 እ.ኤ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመት የቦርድ አባላት ዓመታዊ የስራ ዋጋ እና እ.ኤ.አ

የ2022/2023 ወርሀዊ አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.9  እ.ኤ.አ የ2022/2023 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮች ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.10 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሔድ፣

1.11 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.12 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፣

 1. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

2.1 የጉባዔውን ጽ/ቤት ማቋቋም፣

 • የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
 • ከተከፈለው የኩባንያው ካፒታል እድገት ጋር በተገናኘ የመመስረቻ ጽሁፉን  ማሻሻል፣
 • የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፣

ዋና ምዝገባ ቁጥር አአ/ግማ-3-1703/87

የተከፈለ ካፒታል 646.4 ሚሊየን ብር

 1. ማሳሰቢያ፡-
 • በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ከሆነ በተወካይ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በተወካይ የሚሳተፉ ከሆነ፡-

 • ከጉባዔው ሦስት ቀናት በፊት ጎተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ በግንባር ቀርበው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የውክልና ፎርም ሞልተው እንዲፈርሙ ወይም
 • በሠነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን የያዙ ተወካይ በዕለቱ በጉባዔው ቦታ የውክልና ሠነዱን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
 • ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ