የኔፕ ፕላስ በሲቪል ማህበረሰብ ተለያየ የግንዛቤ ማዳበሪያ መልዕክቶች የተጸፉበት ከቆዳ የተሠራ የላብቶፕ መያዠ ቦርሳ አዘጋጅቶ በሥረው ለተሠማሩ መልዕክተኞች ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡

network-of-networks-of-hiv-positives-logo

Overview

 • Category : Textile & Leather Products Sell & buy
 • Posted Date : 07/23/2022
 • Phone Number : 0116591616
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/12/2022

Description

የቆዳ ቦርሳ ግዥ ጨረታ

ኔፕ ፕላስ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መዝገብ ቁጥር 1483 የተመዘገበ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን በትኩረት ከሚያከናውናቸው የጤና እና የልማት ሥራዎች መካከል አንዱ ኤች አይ ቪ አድስ ስረጭትን መግታት ሲሆን ሥራውንም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ያከናውናል፡፡  

ድርጅታችን የኤች አይ ቪ ምርመራ፣መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ እና የቫይረሱን መጠን ለመቆጣጠር እንዲያመች በማህበረሰቡ ዘንድ ፍላጎትን ለመጨመር የተለያየ ዘዴዎችን በመጠቀም የህዝቡን ግንዛቤ በዘርፉ ለማዳበር ይሰራል፡፡ በዚው መሠረት የተለያየ የግንዛቤ ማዳበሪያ መልዕክቶች የተጸፉበት ከቆዳ የተሠራ የላብቶፕ መያዠ ቦርሳ አዘጋጅቶ በሥረው ለተሠማሩ መልዕክተኞች ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፉ የተሠማሩ ተጫራቾች ለሥረው እንድወዳደሩ ተጋብዟል፡፡

 • የሚቀርበው የቦርሳ ዓይነት (ስፔስፍኬሽን) እንደሚከተለው ነው
  • ከቆዳ የተሠራ የላብቶፕ መያዣ ቦርሳ፤
  • መጠኑ 40×30 CM ሆኖ የተለያየ ከለር ያለው፤
  • ከፊት ለፊቱ በኩል ሁለት ኪሶች ያሉትና ኪሶቹ በጥሩ ሁኔታ  የሚዘጉ፤
  • ውስጡ ቢያንስ ሁለት ክፍሎች ያሉት እና ጠንካራ የሆነ፤
  • ጠንካራ ማንገቻ እንድሁም የእጅ መያዣ ያለው፤
  • በውስጡ የሞባይልና የእስክርብቶ ማስቀመጫ ያለው፤
  • በአንዱ ወገን የድርጅታችን አርማ በቆዳ የሚጻፍ ሆኖ ሌላም አጭር መልዕክት መያዝ የሚችል ፤
 • ተጫራቹ የሚሰራውን የቦርሳ ዓይነት እና ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
  • ብዛቱ 100 ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል፤
 • ምርቱን ከሚያቀርበው ድርጅት የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታዎች
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣TIN ሰርተፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል፤
  • ከተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር በመስራት ልምድ ያለውና በዘርፉ ቢያንስ ከ 2 ዓመት በላይ የሠራ፤
  • ሥራውን የሚያከናውንበትን ጊዜ በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፤
  • ሥራውን የሚያከናውን የሰው ሀብት የማቴሪያል ዝርዝር ያሟላ፤ለዚህም ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል፤
 • ተጫራቾች ድርጅቱ ያወጣውን የጨረታ መመሪያን በሙሉ መከተል አለባቸው፤
 • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ አከባቢ በሚገኘው ድርጅታችን መግዛት ይችላሉ፤
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ.ማስያዝ አለባቸው፤
 • የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በሠም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለባቸው፤
 • የጨረታው ሰነድ ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ህንጻ 5ኛ ፎቅ፤ ድርጅታችን የፋይናንስና አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 405 ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርበታል፤
 • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ 10፡30 ላይ ይከፈታል፤
 • ተጨራቾች ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር (+251)011-659-16-16/1919 ማግኘት ይችላሉ፤
 • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤