የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር በኦኘሬተሮችና አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የስልጠና መስክ ስልጠና የሚሰጡ ባለሙያዎችን ወይም ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Yencomand-Construction-Logo

Overview

 • Category : Education & Training Services
 • Posted Date : 08/17/2022
 • Phone Number : 0115523022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/30/2022

Description

ለኦኘሬተሮችና አሽከርካሪዎች ስልጠና ለመስጠት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ በዋና መ/ቤትና በተለያዩ የመንገድ ስራ ኘሮጀክቶች ተቀጥረው ለሚሰሩ የድርጅቱ ኦኘሬተሮችና አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የስልጠና መስክ ስልጠና የሚሰጡ ባለሙያዎችን ወይም ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡-

 1. በከባድ ማሽነሪዎች ኦኘሬሽን፣ አያያዝና የስራ ላይ ጥንቃቄ፤
 2. በከባድ ተሽከርካሪዎች አያያዝ፣ የማሽከርከር ኃላፊነቶችና የስራ ላይ ጥንቃቄዎች፤
 3. የቀላልና መካከለኛ ተሽከርካሪዎች አያያዝ፣ የማሽከርከር ኃላፊነቶችና የስራ ላይ ጥንቃቄዎች፤
 4. የኦኘሬተሮችና አሽከርካሪዎች የመከላከል፣ ጥገናና ክትትል፤
 5. የኦኘሬተሮችና አሽከርካሪዎች የቴክኒክ ግንዛቤ ማስጨበጥ፤
 6.  ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
  • ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቀርቦ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
  • ተጫራቾች በኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ በቂ ስልጠና መስጠት የሚችሉ፣ ቢያንስ ከ5 ዓመት በላይ በዘርፋ በቂ ልምድ ያላቸውና ለሌሎች መሰል ድርጅቶች ስልጠና የሰጠና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋውን 20% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  “ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡”

  የንኮማድ ኮንስትራክሸን ኃ/የተ/የግል ማህበር

  አድራሻ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ

  ዕቃና አገልግሎት ግዥ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107

  ስልክ ቁጥር 0115523022