የንጋት ሜካኒካል ምሕንድስና አ.ማ. የባለአክሲዮኖች የ17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባ

Announcement
Nigat-Mechanical-Engineering-S.-C.-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/29/2021
 • E-mail : nigatmechanical@gmail.com
 • Phone Number : 0116461545
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/11/2021

Description

ለንጋት የሜካኒካል ምሕንድስና አ.ማ. ባለአክሲዮኖች

የስብሰባ ጥሪ

የንጋት ሜካኒካል ምሕንድስና አ.ማ. የባለአክሲዮኖች የ17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ታኀሣሥ 2 ቀን 2014ዓ.ም. (December 11, 2021) በግዮን ሆቴል አዋሽ የስብሰባ አዳራሽ ከቀኑ 8፡00ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ከላይ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በጉባዔው ላይ እንዲገኙና እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ

የመደበኛ ስብሰባው አጀንዳ

 • የጉባዔውን ረቂቅ አጀንዳዎች ማጽደቅ
 • የዳይሬክተሮች ቦርድን የ2013 በጀት ዓመት ሪፖርትን ማዳመጥ
 • የ2013 የውጪ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ
 • በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ መወያየትና ማጽደቅ
 • የዳይሬክተሮችን አበልና የሥራ ዋጋ መወሰን
 • የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ
 • የስብሰባውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ

በአካል በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች የተረጋገጠ ሕጋዊ የውክልና ሠነድ በያዙ ወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በማክበር እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት አድራሻዎች ይጠቀሙ

ስልክ፣ 0116461545፣ 0930013570 ወይም 0911104469

ኢሜይል፣ nigatmechanical@gmail.com

Send me an email when this category has been updated