የአሮሚያ ባንክ አራዳ ቅርንጫፍ ለአቶ ወርቁ ገነት ለሰጠው ብድር በዋስትና ይዞ የነበረዉንና ተበዳሪው ዕዳቸውን በዉሉ መሠረት መክፈል ባለመቻላቸዉ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለዉ) በተሰጠዉ ሥልጣን መሠረት ባንኩ በዋስትና የያዘዉንና ለብድር ማካካሸነት የወረሰውን የመኖሪያ ቤት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia-international-bank-logo-9

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 12/31/2022
 • Phone Number : 0115572023
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/18/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአሮሚያ ባንክ አራዳ ቅርንጫፍ ለአቶ ወርቁ ገነት ለሰጠው ብድር በዋስትና ይዞ የነበረዉንና ተበዳሪው ዕዳቸውን በዉሉ መሠረት መክፈል ባለመቻላቸዉ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለዉ) በተሰጠዉ ሥልጣን መሠረት ባንኩ በዋስትና የያዘዉንና ለብድር ማካካሸነት የወረሰውን የመኖሪያ ቤት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ የንብረቱም ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡በመሆኑም ህንፃዉን መግዛት የሚፈልጉ ከታች በተገለፀው መስፈርት መሠረት በጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተ.ቁጥር ለጨረታ የቀረበዉ  ሕንአይነት  ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት የጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት 
ከልል ከተማ ቀበሌ/ወረዳ  የካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት በካ.ሜ.
ቀን ሰዓት
1 መኖሪያ ቤት ኦሮሚያ አዳማ 01  

428/99

 

200 6,249,455.16 08-05-2015 8፡30-9፡00
 • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ንብረቱን በሚገኝበት አድራሻ ቀርበዉ ማየት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሠነድ (ሲ.ፒ.ኦ) በአሮሚያ ባንክ ስም አሰርተዉና ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በፅሁፍ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዚህ በታች ባለዉ አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የመወዳደርያ ዋጋቸዉን እና የጨረታ ማስከብረያ ሲ.ፒ.ኦ. በአንድ ፖስታ ዉስጥ በማሸግ እስከ ጥር 08 ቀን 2015 ዓ. ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ጥር 05 ቀን 2015 ዓ. ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የብድር ክትትል እና ማስመስ ዳይሬክቶሬት ክፍል ዉስጥ ይከፈታል፡፡
 • የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠሰዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ገቢ የማይደረግ ከሆነ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
 • የጨረታዉ አሸናፊ ተጫራች የባንኩን የብድር ህግና ደንብ አሟልቶ ከተገኘ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
 • ጨረታዉን ያሸነፈ ተጫራች ለመወዳደሪያ ካቀረበዉ ዋጋ በተጨማሪ ለመንግሥት የሚከፍለዉን አስፈላጊ ግብርና ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ማንኛዉንም ተያያዥ ወጪዎች ይከፍላል፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-57 20 23 ዋና መ/ቤት ወይም በ 0221-119316/17/18 (አራዳ ቅርንጫፍ) ደዉለዉ ማነጋገር ይቻላሉ፡፡
 • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

አድራሻ

አዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ከጌቱ ኮሜርሺያል ሴንተር ጎን የሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት

1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-407-1

ብድር ክትትል እና ማስመለስ ዳይሬክቶሬት

ኦሮሚያ ባንክ