የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 12ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

Announcement
-ባንክ-logo

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 04/19/2021
  • Phone Number : 0115526314
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/29/2021

Description

ለአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 12 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ያልተከፈለ አክሲዮን ያለባቸው ባለአክሲዮኖች በ11ኛ ድንገተኛ ጉባዔ የተወሰነው የመጨረሻ መክፈያ ጊዜ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. እንዲሆን የተወሰነ ቢሆንም፤ ይህ ተሻሽሎ አጠቃላይ ክፍያው እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ እንዲሁም እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ክፍያ ያላጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች ካሉ በባንኩ የፋይናንስና ሒሳብ መምሪያ እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ቀርበው አክሲዮን ለመግዛት ፈቃደኝነታቸውን ለገለጹ ባለአክሲዮኖች ባላቸው የአክሲዮን መጠን ድልድል ተደርጐ ክፍያውን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ ከፍለው እንዲያጠናቅቁ የተወሰነ መሆኑን ይገልፃል፡፡

በመሆኑም የተፈረሙና ያልተከፈሉ አክስዮኖችን አጠናቆ የመክፈያ ጊዜው ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም  እሁድ ቀን የሚውል በመሆኑ ባለአክሲዮኖች በ11ኛ ድንገተኛ ጉባዔ መሠረት የፈረሙትን የአክሲዮን ድርሻና እስካሁን ዋጋቸው ያልተከፈሉ አክሲዮኖች ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቀው፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በባንኩ የፋይናንስና ሒሳብ መምሪያ በመቅረብ ክፍያውን በሙሉ በመፈጸም እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን የማያጠናቅቅ ባለአክሲዮን ዋጋቸው ያልተከፈሉት የአክሲዮን ድርሻውን፣ አክሲዮኖች ለመግዛት ለሚፈልጉ ነባር ባለአክሲዮኖች በ12ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሣኔ መሠረት የሚተላለፍ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

ከላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተፈረመው ክፍያቸው ያልተጠናቀቁ አክስዮኖችን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ነባር ባለአክስዮኖች እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በባንኩ የፋይናንስና ሒሳብ መምሪያ በአካል በመቅረብ ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን የፍላጎት ማሳወቂያ ቅፅ እንድትሞሉ እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 526314 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ

አዲስ አበባ