የአቢጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ አክስዮን ማኅበር በፋብሪካው ከልዩ ልዩ ሥራዎች የተረፉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Steels & Aluminium supply & sale
 • Posted Date : 12/24/2022
 • Phone Number : 0113205602
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/30/2022

Description

የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የአቢጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ አክስዮን ማኅበር በፋብሪካው ከልዩ ልዩ ሥራዎች የተረፉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሁኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡

 1. ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ቫት ተመዝጋቢ የሆነና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይኖርበታል፡፡
 2. ተጫራቾች ብረታብረቶቹ ወደ ሚገኙበት የአክስዮን ማኅበሩ ፋብሪካ ከዝዋይ (ባቱ ) ከተማ ወደ ሻሸመኔ በሚወስደው መንገድ 25 ኪ.ሜ እርቆ በሚገኘው ቡልቡላ ከተማ ወደ ቀኝ ገባ ብሎ ባለው ወደ ቀድሞው የሕፃናት አምባ በሚወስደው 5 ከ.ሜ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላው ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም C.P.O ቼክ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት C.P.O ቼኩ ወይም ጋራንቲው ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች በሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጉርድ ሾላ በሚገኘው በኤልፎራ አግሮ ኢዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ባለው የአክስዮነ ማኅበሩ ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
 7. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 ቀናት ውስጥ ሙሉውን ዋጋ ከፍሎ ብረቶቹን ካልወሰደ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ በቅጣት መልክ ለአክስዮን ማኅበሩ ገቢ ሆኖ ከጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛላ ፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 9. አክስዮን ማኅበሩ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማረ መረጃ

አቢጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ አክስዮን ማኅበር

ጉርድ ሾላ ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ

የስልክ ቁጥር 0113205602፣0113712908 ወይም 0913151615