የአወሊያ አርዳታና ልማት ድርጅት ያገለገሉ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 08/24/2022
 • Phone Number : 0112708158
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/31/2022

Description

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የአወሊያ አርዳታና ልማት ድርጅት ያገለገሉ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመወዳድር ለምትፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች፡ 

  1.የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ዋና ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር147C23000023 አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ስም በማስገባት ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች በአካል በመገኘት የመኪናዎችን ይዞታ በመመልከት ደርጅቱ ባቀረበው የመነሻ ዋጋ ላይ መግዛት የምትችሉበትን ዋጋ በተናጠልና በጥቅል ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ትክክለኛ ስማቸውንና አድራሻቸውን በጨረታ ሰነዳቸው ላይ በመፈረም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የሚገዙበትን ንብረት ለእያንዳንዱ ሎት/መደብ ለጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ /10% ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣው ከተጠቀሰበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ግቢ በአወሊያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
 4. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጠላቸው 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ሙሉ ዋጋውን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ዋጋውን መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተድርጎ እድሉ ለሁለተኛ አሸናፊው የሚሠጥ ይሆናል፡፡ 
 5. የጨረታ ማስገቢያው ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣጽ ጊዜ ጀምሮ ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት በድርጅቱ የስራ ቀናት መሰረት ይሆናል፡፡
 6. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው በመክፈል መኪኖችን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
 7. ቦታው አዲስ አበባ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፤ወረዳ 05 ከጀኔራል ዊንጌት ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ አለፍ ብሎ በሚገኘው ልዩ ቦታው አወሊያ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ሲሆን ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈልገ በስልክ ቁጥር 0112708158 ወይም 0112707916 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት