የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት ከሚያርዳቸው እንስሳት የሚገኘውን የተለያዩ ተረፈ-ምርቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Addis-Ababa-Abattoirs-Enterprise-logo

Overview

 • Category : Agriculture Farm Products
 • Posted Date : 05/20/2021
 • Phone Number : 0114163968
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/03/2021

Description

የተለያዩ የእንስሳት ተረፈ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት ከሚያርዳቸው እንስሳት የሚገኘውን የተለያዩ ተረፈ-ምርቶች ማለትም የዳልጋ ከብት የሽሆና ጅማት፣ ቁርዝ፣ ቀንድ፣ ሀሞት፣ የልብቧንቧ፣ የግንባር ቆዳ፣ ጅማቱ የወጣለት ጥሬ ሽሆና አጥንት፣ ትንሹ አንጀት፣ የበሬቴስቲክል፣ የሽሆና ጥፍር እና የበግና የፍየል አንጀት፣ ቴስቲክል፣ ቁርዝ፣ የግመል ቆዳ፣ እና ሌሎች ወደፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፁ ተረፈ ምርቶችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-

 • በመስኩ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈለ የማይመለስ ኮፒ በማያያዝ ማቅረብ አለበት፡፡
 • የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የዳልጋ ከብት ተረፈ-ምርቶች ብር 100,000 /አንድመቶሺህብር/ እና ለእያንዳንዱ በግና ፍየል ተረፈ-ምርቶች ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በድርጅቱ ጥሬ ገንዘብ መሠብሠቢያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
 • የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መውሰድ ይችላል፡፡
 • የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለበት፡፡
 • ጨረታው ሰኔ 3 ቀን 2013ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በ0114163968/78 ይጠይቁ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት

Send me an email when this category has been updated