የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

Addis-Ababa-Abattoirs-Enterprise-logo-1

Overview

  • Category : Purchases
  • Posted Date : 07/30/2022
  • Closing Date : 08/16/2022
  • Phone Number : 0114652294
  • Source : Reporter

Description

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2014

የአዲስ አበባ  ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

  1. የተለያዩ የፅህፈት መሣሪያዎች እና የተለያዩ የኮምፒተር መለዋወጫዎችና ቶነሮች፣
  2. -NETWORK ATTACHED STORAGE-(NAS)
  3. የፅዳት ዕቃዎች እና የምርት መገልገያ ዕቃዎች(ጋሪ፣ አካፋ፣…)
  4. የምርት ማሸጊያ ማዳበሪያ፣ የማዳበሪያ መስፊያ ክር፣የድርጅቱ አርማ ያለበት የውሻ መኖ ማሸጊያ፣ የሸሆና ማሸጊያ ፕላስቲክ ከረጢት
  5. የደንብ ልብስ ስፌት ከነጨርቁ፣ ሸሚዝ፣ 6000 ሰማያዊ ቴትሮን ቢጫ ካኪ ጨርቅ ስማያዊ ካኪ ጨርቅ ፖሊስተር 6ዐዐዐ ነጭ ብትን ጨርቅ ፣ የሴቶች ቆዳ ጫማ፣ የወንዶች ቆዳ ጫማ፣ ሴፍቲ ሹዝ/ጫማ/፣ ኘላስቲክ ቦት ጫማ፣ የቆዳ ሽርጥ፣የካባ ቤርጋሞድ እና የሙቀት ሹራብ የፊት ፣ሽርጥ ቤርጋሞድ፣ ፕላስቲክ የእጅ ጓንት ፣የዝናብ ልብስ
  6. የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች
  7. የተለያዩ መጠን ያላቸው ብረታ ብረቶች
  8. የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  9. የተለያየ መጠን ያላቸው የተሽከርካሪ ጐማዎች ፣ የተሽከርካሪ በልቦች እና የተሸከርካሪ ባትሪዎች
  10. የተለያዩ የቴክኒክ መገልገለያ እቃዎች
  11. የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት፣
  12. ለህንፃ ግንባታ እና ጥገና የሚያገለግሉ የተለያዩ ዕቃዎች፣
  13. የበሬ ላይ ቁጥር መፃፊያ ሰማያዊ ቀለም እና የተለያዩ አይነት የህንፃ ቀለሞች፣
  14. የባለሙያ ወንበር፣ የፀሐፊ ወንበር፣ የእንግዳ ወንበር፣ፋይል ካቢኔት
  15. EGA 500*200*4MM፣EGA 500*400*4MM፣ EGA 500*300*4MM

ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የቲን ሰርተፍኬት ያለው፡፡
  • ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3ዐ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፣
  • የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
  • ጨረታው ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡3ዐ ሰዓት  የሁሉም  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11-4-65 22 94 /ዐ11 4 66 75 ዐ1 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት