የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በ20/80 ፕሮግራም በቦሌ ቡልቡላ፣ በለሚ ኩራ፣ በአራዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ያስገነባቸውን 2,667 ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡

Commercial-Nominees-logo-1

Overview

  • Category : House & Building Sale
  • Posted Date : 07/17/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 08/11/2022

Description

ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በ20/80 ፕሮግራም በቦሌ ቡልቡላ፣ በለሚ ኩራ፣ በአራዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ያስገነባቸውን 2,667 ኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት የጨረታ ሰነዱን  ከሃምሌ 11 እስከ ነሃሴ 04/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) የስራ ቀናት፣  ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡10 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ) ብር በመክፈል ሰነዱን ከሚከተሉት አድራሻዎች መግዛት ይችላል፡፡

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ሥፍራዎች

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር በገባው ውል መሰረት የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው በ9 (ዘጠኝ) የተለያዩ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ቅርንጫፎች ሲሆን አድራሻቸው እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ ሰነዱ የሚሸጥበት ቅርንጫፍ የሰነድ መሸጫ ስፍራ (ቅርንጫፉ የሚገኝበት አድራሻ) ስልክ ቁጥር
1. ልደታ ቅርንጫፍ ተ/ሀይማኖት አሰብ ሆቴል ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚገኝበት ህንፃ 1ኛ ፎቅ 0111-55-98-61
2. አራዳ ቅርንጫፍ ፒያሳ አራዳ ህንፃ 1ኛፎቅ 0111-57-79-83
 

3.

ሳሪስ ቅርንጫፍ ሳሪስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ (ሪየስ ኢንጂነሪንግ ፊት ለፊት) ወይም ቀይ መስቀል መድኃኒት ቤት ጎን 0114-42-57-83
4. ቂርቆስ ቅርንጫፍ ልደታ ማርያም ቤ/ክ ከፍ ብሎ ዛግዌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት 0114-66-36-36
5. የካ ቅርንጫፍ ላምበረት ሾላ ወተት ፋብሪካ ፊት ለፊት  የሚገኝ ህንፃ ላይ 0116-68-31-02
6. መገናኛ ቅርንጫፍ ገርጂ ጃክሮስ አደባባይ በኮብል ስቶን 100 ሜትር ገባ ብሎ ሾላ አፓርትመንት አጠገብ (ቀደም ሲል ማክሚላን አካዳሚ የነበረበት ህንፃ) 0116-62-57-76
 

7.

ኮልፌ ቅርንጫፍ ኮልፌ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጵ/ቤት የሚገኝበት ህንጻ 3ኛ ፎቅ (ጦር ሀይሎች ሆላንድ ኢምባሲ) 011384-20-00
8. መርካቶ ቅርንጫፍ መሀል መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 0112-13-23-26
9. ኮሜርሻል ኖሚኒስ ዋናው መስሪያ ቤት ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ የብሄራዊ አደጋ ስጋትና ዝግጁነት ኮሚሽን መስሪያ ቤት አጠገብ ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ 09-74-41-68-78

09-70-74-41-78

  • የጨረታ ማጠናቀቂያ ቀን፡– ነሃሴ 04/2014 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  • የጨረታ መክፈቻ ቀን፡ነሃሴ 05/2014 ዓ.ም እስከ ነሃሴ 17/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ፕሮጋራም መሰረት ይሆናል፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶቸ ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን