የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በንግድ ዕቅድ ዝግጀት እንዲሁም በስራ ፈጠራ ልማት ዙሪያ  በቂ እውቀት ባላቸው አማካሪዎች  የማማከር አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

Addis-Ababa-chamber-of-Commerce-and-Sectoral-logo-1

Overview

 • Category : Baseline Consultancy
 • Posted Date : 06/11/2021
 • E-mail : addischamber@gmail.com
 • Phone Number : 0115500934
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/21/2021

Description

ADDIS ABABA CHAMBER OF COMMERCE & SECTORAL ASSOCIATIONS

የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የማማከር አገልግሎት የድጋፍ ዕድል

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከጀርመን ቴክኒካ(ል)ዊ ትብብር (Giz)  ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ስራ ፈጠራን ለማሳደግ እና የቢዝነስ ተቋማትን ለማበረታታት  የ18 ወራት ፕሮጀክት ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ 

በዚህም መሰረት ለድጋፍ ከተመረጡ የስራ ዘርፎች አንዱ ግብርና ሲሆን፤በዚህም ዘርፍ በግብርና ተዋፅኦ ያሉትን የእሴት ሰንሰለት  እድሎች  ላይ አፅኖት በመስጠት ይሰራል። ለድጋፍ ከተመረጡ መስኮች መካከል በግብርና ምርት ዘርፍ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በንግድ ዕቅድ ዝግጀት እንዲሁም በስራ ፈጠራ ልማት ዙሪያ  በቂ እውቀት ባላቸው አማካሪዎች  የማማከር አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በፕሮግራሙ ላይ መሳተፍ የሚችሉት  በዋነኝነት በአግሪ ቢዝነስ  ላይ የተሰማሩ ማለትም የግብርና ምርቶችን  የሚያመርት፣ ምግብ ነክ ነገሮችን የሚያቀነባብር እና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን የሚያመርት ወይም የግብርና ምርቶችን በመሸጥ፣በማከፋፈል የተሰማሩ እንዲሁም  በግብርና ምርቶች ዙሪያ አዲስ ንግድ ለመጀመር/ለማቋቋም በሂደት ላይ ያሉ ሲሆኑ በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-

 1. በአግሪ ቢዘነስ ላይ የተሰማራ፣
 2. በአነስተኛ ወይም መካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ንግዶች ፣
 3. አገልግሎቱን  ሳያቋርጡ ለመከታተል እና ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛነትን የሚያሳይ የተፈረመ የማመልከቻ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ፣
 4. የንግድ ምክር ቤቱ አባል ለሆኑ ቅድሚያ ይሰጣል፣
 5. ቢያንስ 10 ክፍል ያጠናቀቀች/ቀቀ፣
 6. በሴቶች እና በወጣቶች የሚመራ ድርጅት ይበረታታል፣
 7. የድጋፍ ማስረጃ ለምሳሌ መታወቂያ፣ የንግድ ፍቃድ …ማቅረብ የሚችል፣

 በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ

ከዚህ በታች የተመለከተውን የማመልከቻ  ፎርም በመሙላት ሜክሲኮ በሚገኘው አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ቢሮ ቁጥር 6  በአካል በመገኘት ወይም በኢሜል አድራሻ፦ addischamber@gmail.com  እሰከ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲመዘገቡ እየጠየቅን፣  

በተጨማሪም በስልክ ቁጥር ፡ 0115-500934 ወይም 0115-518055 በውስጥ መስመር 226 በመደወል መረጃ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

ቀን: _________________________________________________________________

የድርጅት ስም : _____________________________________________________________

የተሰማሩበት የስራ መሥክ: __________________________________________________

የተሳታፊ ስም/ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጅ/: ___________________________________

የስራ ድርሻ: _________________________________________________________________

ስልክ ቁጥር: ________________________________________________________________

ኢሜይል: _________________________________________________________________