የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራ ምክር ቤት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Addis-Ababa-chamber-of-Commerce-and-Sectoral-logo

Overview

 • Category : Disposal Sale
 • Posted Date : 04/03/2021
 • Phone Number : 0115518055
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/20/2021

Description

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክርቤት

Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations

ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ

 

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራ ምክር ቤት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡

 1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ አካል ማንነቱን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ወይም ንግድ ፈቃድ ኮፒ በመያዝና ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ  ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሜክሲኮ ከሚገኘው የምክር ቤቱ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይችላል፡፡
 2. ንብረቶቹን ማየት የሚፈልግ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ጨረታው እስከሚከፈትበት ባሉት የስራ ቀናት  ከሰኞ እስከ አርብ  ሜክሲኮ በሚገኘው ቢሮ በመምጣት ማየት ይችላል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. በጨረታው የሚሳተፈው ግለሰብ ከሆነ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
 5. የጨረታ ሰነዱ የሚቀርበውና ሲፒኦ የሚሰራው የጨረታ ሰነዱን በገዛው ግለሰብ/ድርጅት ብቻ ይሆናል ፤ የጨረታ ሰነዱን የገዛውና የጨረታ ሰነዱ የቀረበው በተለያየ ስም ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለምክር ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 7. ተጫራቾች ለተሸከርካሪዎች የሠሌዳ ቁጥር በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ላይ በግልፅ በመፃፍ እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ  4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 10 ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል
 8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን መኪና የአሸናፊነት ማሳወቂያ ደብዳቤ በደረሳቸው በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው መውሰድ አለባቸው፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ገንዘብ ለምክር ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 9. አሸናፊዎች ለሚገዙት መኪና የስም ማዛወሪያ እና ተያያዥ ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
 10. ምክር ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አዲስ አበባ ንግና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

ፖ.ሣ.ቁ 2458

የስልክ ቁጥር  +251 11 551 8055  ፋክስ  +251 11 551 1479

ሜክሲኮ አደባባይ፣ ንግድ ምክር ቤት ህንፃ፣ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

Send me an email when this category has been updated