የአዲስ አበባ የገበያ ማዕከል መርካቶ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 28ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 10/22/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/06/2022

Description

ለአ/አ የገበያ ማዕከል መርካቶ አ/ማ አባላት በሙሉ

አዲስ አበባ 

ጉዳዩ፡- የባለ አክሲዮኖች ዓመታዊ የስብሰባ ጥሪ

የአዲስ አበባ የገበያ ማዕከል መርካቶ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 28ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እሁድ ህዳር 4 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል ሀረር ግሪል አዳራሽ ስብሰባውን ስለሚያካሂድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የገበያ ማዕከሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

    የስብሰባ አጀንዳ

  1. የዕለቱን አጀንዳ ማጸደቅ፣
  2. የዳሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማቅረብ፣
  3. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማቅረብ፣
  4. በቀረቡት ሁለቱ ሪፖርቶች መወያየትና ማጽደቅ

5 የትርፍ ክፍፍልን መወሰን፣

ከሠላምታ ጋር

ማሳሰቢያ

  • በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ አንድ ቀን በፊት በማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ቢሲ 4ዐ1 በመቅረብ የውክልና ፎርም ሞልተው ውክልና መስጠት ወይም የፍርድ ቤት ውክልና በመያዝ ተወካዩም የተሰጣቸውን የውክልና ማስረጃ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የኦዲት ሪፖርቱን ለግንዛቤ እንዲረዳ ከጥሪው ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን ልከናል፡፡