የአፍሪካ የቆዳና  ቆዳ  ውጤቶች ኢንስቲትዩት  ሲጠቀምበት  የነበረውን በጃፓን  አገር  በ1994 የተመረተ ቶዮታ ሚኒባስ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ  ይፈልጋል ፡፡

Africa-leather-and-leather-product-institute-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 09/09/2021
 • Phone Number : 0114390228
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/20/2021

Description

አፍሪካ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንስቲትዩት

የአፍሪካ የቆዳና  ቆዳ  ውጤቶች ኢንስቲትዩት  ሲጠቀምበት  የነበረውን በጃፓን  አገር  በ1994 የተመረተ ቶዮታ ሚኒባስ የታርጋ ቁጥር ዕድ 6-002 ሞዴል RZH114 የሻንሲ ቁጥር RHZ114-7000557 እና የሞተር ቁጥር 1RZ-0640471 የሆነ  ቶዮታ ሚኒባስ ተሽከርካሪ እና ካሚንስ ፓወር ጀነሬተር 2008 የአሜሪካ ምርት  ሞዴል ES17D5, Engine No. 25087,Serial No. H081005394, Stand by KVA 17 ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ  ይፈልጋል ፡፡

 1. መኪናውን  እና  ጀነሬተርሩን ያሉበትን  ሁኔታ  ማየት  የሚፈልጉ  ተጫራቾች  በመስሪያ  ቤቱ  (ቃሊቲ ማሰልጠኛ ወደ ደብረዘይት በሚወስደዉ መንገድ አቃቂ   ቃሊቲ   ክፍለ ከተማ  ወረዳ 05 አካባቢ ሲደርሱ ወደ ግራ ታጥፎ  1  ኪሎ   ሜትር ወደ ዉስጥ  ገባ ብሎ  ከቆዳ ኢንዱስትሪ  ልማት  ኢንስቲትዩት  ፊት  ለፊት)  ቅጥር  ግቢ በስራ ሰዓት  በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
 2. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን  የተሽከርካሪውን እና  ጀነሬተርሩን ዝርዝር   የያዘውን ፎርም  ከላይ ከተገለፀው መስሪያ ቤት ከመስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ  መውሰድ  ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ  ኤንቨሎፕ  እስከ  መስከረም  10 ቀን 2014    ዓ.ም   ከቀኑ  10፡00  ሰዓት   ድረስ  ከላይ  በተጠቀሰው   ቦታ  ለዚሁ  በተዘጋጀው  ሳጥን  ውስጥ  ማስገባት  ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች  ለሚጫረቱበት  ተሽከርካሪ እና  የጀነሬተር   የመነሻ  ዋጋ  25%  (ሀያ አምስት በመቶ) የጨረታ  ማስከበሪያ   በባንክ  ክፍያ  ማዘዣ (CPO) ማስያዝ  ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው  የተሸነፉ ተጫራቾች  በማስያዣነት  ያስያዙት ገንዘብ  ወዲያውኑ ተመላሽ  ይደረግላቸዋል፡፡ (CPO መዘጋጀት ያለበት በ Africa Leather and Leather Products Institute) ስም ይሆናል፡፡
 5.  ጨረታው  ማክሰኞ  መስከረም  11 ቀን 2014 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኢንስቲትዩቱ  ቅጥር ግቢ ዉስጥ  ተጫራቾች  ወይም ሕጋዊ  ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት  ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ እና ጀነሬተር  ሙሉ ክፍያ በ5 ቀናት  ውስጥ  መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ክፍያውን    ከፈፀሙ  በኋላ  በ10 ቀናት  ውስጥ  መኪናውን እና ጀነሬተርሩን ካላነሱ  ለሀያ  ቀናት  በየቀኑ  ብር  30.00 (ሰላሳ ብር) የማቆሚያ ቦታ ኪራይ  የምናስከፍል  ሲሆን  በእነዚህ  ቀናት  ውስጥ ከፍለው  ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ሆኖ  አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
 7. በጨረታው  በቀረበው  ተሽከርካሪ እና ጀነሬተር  ላይ  የሚፈለግ  ማንኛውም  አይነት  የስም  ማዛወርያ፤  ቀረጥ፤  ግብርና  ልዩ  ልዩ   ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡
 8. ለተጨማሪ  መረጃ   በስልክ  ቁጥር 011-4390228/0911233099 /0911952732 በመደወል  ወይም  በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው  አድራሻ  በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይችላል፡፡
 9. መስርያ ቤቱ  ጨረታውን በከፊልም  ሆነ በሙሉ  የመሰረዝ  መብቱ  የተጠበቀ  ነው፡፡
 10.  ሌሎች  ተጫራቾች  ባቀረቡት  ዋጋ  ላይ  ተንተርሶ ዋጋ  ማቅረብ  ክልክል ነው፡፡
 11.  ኢንስቲትዩቱ   የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው  አይገደድም፡፡