የኢቴክ አክሲዮን ማህበር ባለአክስዮኖች የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

Announcement

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/26/2022
 • Phone Number : 0903111177
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/19/2022

Description

የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

ለተከበራችሁ የኢቴክ አክሲዮን ማህበር ባለአክስዮኖች

የኢቴክ አክሲዮን ማህበር  በንግድ ምዝገባ ቁጥር BL/AA/30022713/2013 ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 2 የቤት ቁጥር አዲስ፣ ቦሌ ጃፓን ታምራት ህንፃ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ላይ የሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366፣ 367፣ 370፣ 371 እና 372 መሠረት 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ የባላክሲዮኖች ጉባዔውን ቅዳሜ- ሕዳር 10 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ አትላስ በሚገኘው ማግኖሊያ  ሆቴል አዳራሽ የሚያካሂድ በመሆኑ ባለአክሲዮኖች ከላይ በተጠቀሰው ቀን፣ቦታና ሰዓት በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት ተገኝታችሁ  በጉባዔው እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።

ሀ. የ 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. አጀንዳ ማጽደቅ
 2. የ2014 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፤
 3. የ2014 በጀት ዓመት የዉጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ፤
 4. በተ.ቁ. 2 እና 3 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 5. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል
 6. የተጓደሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥና ማሟላት
 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበልን መወሰን
 8. 2015 በጀት አመት የውጭ ኦዲተርን መሾምና አበል መወሰን
 9. የጉባኤዉን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ፤ ሲሆኑ

ለ. የባአክሲዮኖች 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. አጀንዳ ማጽደቅ
 2. መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብን ማሻሻል
 3. የጉባኤዉን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ

ማሳሰቢያ፤

 1. ባለአክሲዮኖች በጉባኤው ለመሳተፍ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
 2. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች እስከ ህዳር 05 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ቦሌ ጃፓን በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ ሼር ክፍል ቀርበው የውክልና መስጫ ቅፅን እንዲፈርሙ ያስፈልጋል፡፡
 3. በተጨማሪም የውክልና ቅፅ ዋናው ቢሮ መተው ያልሞሉ ባለአክሲዮኖች ውል ለመዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በስብሰባው ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ የተሰጣቸው ወኪልዎ የወካዩን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሃገር ዜጋ መሆንዎን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፤ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ኮፒ እንዲሁም የውክልናውን ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ በስብሰባው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ጃፓን በሚገኘው ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር

+251118-22-04-22 Mobile: 251903111177 | Email: shares@etechsc.com Website: www.etechsc.com

LinkedIn: eTech S.C. | Facebook: eTech S.C. | Twitter: eTech S.C. | Telegram: eTech S.C.

የ ኢቴክ አ.ማ

የዲሬክተሮች ቦርድ