የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ አምራቾችን /አከፋፋዮችን አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በአንድ ዓመት በሚጸና በማዕቀፍ ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Industrial-Inputs-Development-Enterprise-Logo-3

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Phone Number : 0113692439
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/14/2022

Description

የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት

የሸቀጥ ግዥ ጨረታ (ቁጥር 008/2015)  

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ አምራቾችን /አከፋፋዮችን አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በአንድ ዓመት በሚጸና በማዕቀፍ ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 • መደበኛ የቤት ክዳን ቆርቆሮ (CES 40:2021)
 • የግድግዳ ቀለም የውሃ (የተለያየ ዓይነት)
 • የግድግዳና የቆርቆሮ ምስማር (ES 95:2001)
 • ፓስታና ማካሮኒ (ES 1055:2016)
 • ለዳቦ አገልግሎት የሚውል የስንዴ ዱቄት (ES: 1052:2005)
 • በስመቲ ሩዝ ረጅሙ (ናሙና መቅረብ ይኖርበታል)
 • የገላ መታጠቢያ ሳሙና (CES 44-2013)
 • የመፀዳጃ ቤት ወረቀት (ES 1129:2005)
 • የዕቃ ማጠቢያ ሳሙና (CES 120:2013)
 • A-4 የፕሪንተር ወረቀት 80 ግራም (ES ISO 216:2016)
 • የተለያየ መጠን ያላቸው የተርማል ወረቀቶች
 • የፎም ፍራሽ
 • የተለያየ መጠን ያላቸው የብርድ ልብሶች
 • የተለያየ መጠን ያላቸው አንሶላዎች

ስለዚህ በማዕቀፍ ግዥ ጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርቴፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
 2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ ምርት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታው በተመሳሳይ ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት

ስልክ ቁጥር 0113692439