የኢትዮጲያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-public-health-association-logo

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 10/24/2022
  • Phone Number : 0114166041
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/22/2022

Description

ያገለገሉ እቃዎች

ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጲያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዕቃዎቹን  መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር100 (ብር አንድ መቶ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላዎር በሚወስደው መንገድ ከሌጎ ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኝው የኢትዮጲያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በመውሰድ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል፡፡

1.ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ እቃዎች በቀበና ሼል ፊትለፊት ማህበሩ እያስገነባ ካለው ህንፃ መጋዘን እና ከደምበል ወደ መስቀል ፍላዎር በሚወስደው መንገድ ከሌጎ ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኝው ዋና መስሪያ ቤት በአካል ተገኝተዉ በማየት ዋጋቸዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ህዳር 27 /2015 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው የማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ፡፡

  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ያገለገሉ እቃዎች የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታዉ በተመሳሳይ ቀን ህዳር 27/2015 ጠዋት 4፡00 ሰአት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  3. አሸናፊው የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ከፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለማህበሩ ገቢ ይደረጋል፡፡

5.ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተ.ቁ የዕቃዉ አይነት ንብረቶቹ ያሉበት ሁኔታ ብዛት
1 የኮምፒዉተር ሞኒተር ያገለገሉ 48
2 ላፕቶፕ ኮምፒዉተር ያገለገሉ 36
3 ሲፒዩ ያገለገሉ 50
4 ተሸከርካሪ ወንበሮች፤ጠረጼዛና ሸልፍ ያገለገሉ 130
5 በተለያየ መጠን የተሸከርካሪ ጎማዎችእና ከመነዳሪዎች ያገለገሉ 63
6 ዩፒኤስ፤ፕሪንተር እና ሌሎች እቃዎች ያገለገሉ 76
7 ቁርጥራጭ ብረቶች እና ፕላስቲኮች ያገለገሉ 82

የኢትዮጲያ ጤና አጠባበቅ ማህበር

ፖ.ሳ.ቁ 7117፤ ስልክ 0114166041፤

አዲስ አበባ