የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ ጨረታ /ሐራጅ/ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 09/21/2021
- Phone Number : 0115245373
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/28/2021
Description
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ ጨረታ /ሐራጅ/ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተበዳሪው/
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት አድራሻ | የንብረት ዝርዝር | የቦታ ስፋት | የሃራጁ መነሻ
ዋጋ (በብር) |
የሐራጁ
ደረጃ |
የሐራጁ ቀንና
ሠዓት |
ኢቱር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | አዳማ ከተማ፣
መልካ አዳማ ቀበሌ |
ግንባታዎች፤ የመስሪያ ማሽኖች፣ተሽከርካሪዎች፣ መለዋወጫዎች፣ ጥሬ እቃ እና የተመረቱ ምርቶች | 10ሄክታር | 1,132,770,521.25 (አንድ ቢሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ሺህ አምስት መቶ ሃያ አንድ ብር ከ25/100) | ሁለተኛ | ጥቅምተ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ ፤
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- ሐራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች ብቻ በተገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በኦሮሚያ ክልል፣ምስራው ሸዋ ዞን፣አዳማ ከተማ፣ መልካ አዳማ ቀበሌ በሚገኘው የፋብሪካው ቦታ ነው:: በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
- አንዳንድ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች፣ማምረቻ መሣሪያዎች፣ወዘተ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል ::
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊስ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ሥራ የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል:: ነገር ግን በከፊል ብድር ለመግዛት የጨረታ አሸናፊው በራሱ ስም ወይም እራሱ 10%/አስር በመቶ/ ወይም ከዚያ በላይ የአክሲዮን ባለድርሻ የሆነበት የንግድ ማህበር ከግብር፤ከታክስና ከሌሎች ማናቸውም ዕዳዎች ነፃ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ምንም ዓይነት የዕዳ ይከፈለኝ ጥያቄ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት II በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ