የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት ያስመዘገባቸውንና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን የእርሻ ፕሮጅክቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Development-bank-of-Ethiopia-logo-3

Overview

 • Category : Industry & Factory Foreclosure
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Phone Number : 0115522468
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/03/2023

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት ያስመዘገባቸውንና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን የእርሻ ፕሮጅክቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪው/መያዣ

  ሰጪው ሥም

 የንብረቱ አድራሻ   የንብረት ዝርዝር የቦታው ስፋት

በሄክታር

 የሐራጁ መነሻ

  ዋጋ በብር

የሐራጁ

ደረጃ

 

 ሐራጁ የሚካሄድበት 

   ቀንና ሰዓት

1. ጂ.ጂ.ኤፍ ኢንትግሬትድ ፕሮዳክሽን ፋርም ኃ/የተ/የግል ማህበር በሶማሌ ብ/ክ/መ ሸበሌ ዞን አዳድሌ ወረዳ ጃሬ ቀበሌ የጥጥና ሽንኩርት የመስኖ እርሻ ልማት&ግንባታዎች&

ማሽነሪዎችና የለማ መሬት

   300

 

11,951,074.50

 

 አንደኛ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም

ከጥዋቱ 4:00-6:00

 

2.

ማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መ’አኙዋ ዞን’መንገሺ ወረዳ’ ›i’@“ ባያ kuK?  የሙዝ እርሻ ልማት&

ግንባታዎች&

የእርሻ ማሽነሪዎች እና

ተሽከርካሪዎች

1000/ ከዚህ ውስጥ ከፊሉ በሙዝ ተክል የለማ/ 241,180,405.31   አንደኛ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም

ከጥዋቱ 4:00-6:00

 

 

ማሳሰቢያ&

 • ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
 • አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ድርጅቱን ድጋሚ ለሐራጅ በሚቀርብበት ጊዜ ባንኩ ለሚያወጣው ወጪና በሚደርስበት ኪሳራ ይጠየቃል፡፡
 • ሐራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው’ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ በተገኙበት ይሆናል፡፡
 • በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 • 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
 • የፕሮጀክቱ የምርት መሣሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ወዘተ ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑ የጨረታው አሸናፊ ከተበዳሪው ጋር ተመሳሳይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ አልያም የሚጠበቅበትን የመንግስት ቀረጥና ታክስ ይከፍላል፡፡
 • ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊስ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን በከፊል ብድር ለመግዛት የጨረታ አሸናፊው በራሱ ስም ወይም እራሱ 10%/አስር በመቶ/ ወይም ከዚያ በላይ የአክሲዮን ባለድርሻ የሆነበት የንግድ ማህበር ከግብር፤ከታክስናከሌሎች ማናቸውም ዕዳዎች ነፃ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ምንም ዓይነት ይከፈለኝ ጥያቄ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
 • ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-552-24-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
 • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                                                                       የኢትዮጵያ ልማት ባንክ