የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/11 መሰረት ባልተከፈለው የብድር ገንዘብ ማካካሻነት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Development-bank-of-Ethiopia-logo-4

Overview

 • Category : Other Foreclosure
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Phone Number : 0115245373
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/21/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/11 መሰረት ባልተከፈለው የብድር ገንዘብ ማካካሻነት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተ/

የተበዳሪው/የመያዣ

ሰጪው ስም

የንብረት አድራሻ የንብረት ዝርዝር የቦታ ስፋት

(በሄክታር)

የጨረታ መነሻ

ዋጋ (በብር)

የጨረታሁኔታ የጨረታ

ደረጃ

ጨረታው

የሚካሄድበት

ቀንና ሰዓት

 

1

 

ሩቺ አግሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ

መንግስት፤ አኙዋክ ዞን፣

ጎግ ወረዳ፣ ፑኚውዶ ቀበሌ

ግንባታዎች፤ ተሽከርካሪዎች፣ የእርሻ መሳሪያዎች እና መሬት ልማት 5,199  

91,489,527.03

 

ዝግ ጨረታ

 

 

ሁለተኛ

 

 

ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

 

2

ቢ.ኤች.ኦ ባዮ ፕሮዳክትስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ

መንግስት፤ ኢታንግ ልዩ

ወረዳ፣ ዋትጋች ቀበሌ

የእርሻ መሬት ከነሙሉ መሽነሪዎች እና ግንባታዎች 5,000  

 

61,488,959.48

 

ድርድር

 

አንደኛ

 

3

 

 

ይጋርሰሀዱታ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

የማር ማቀነባበሪያው በጋምቤላ

ብሄራዊ ክልላዊ

መንግስት፣ ማጃንግ ዞን፣ ጉደሬ

ወረዳ፣ ሜጢ ከተማ፡፡

የንብ እርሻ ልማት ፕሮጀክቱ

በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ

መንግስት፣ ማጃንግ ዞን፣

መንጋሺ ወረዳ፣ አሽኔና ባያ

ቀበሌ

 

ማሽነሪዎች ፣ የፋብሪካ ግንባታዎች፤ የመኖሪያና  መጋዘን ህንፃዎች እና  ተሸከርካሪዎች

 

 

1.5 የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እና 500 የንብ ማነብ ቦታ  

 

 

36,875,434.62

 

 

 

ድርድር

 

 

 

ልዩ ድርድር

 

 

ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ሰዓት

 

4

ኢቱር ቴክስታይል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ

መንግስት በአዳማ ከተማ

መልካ አዳማ ቀበሌ

ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ተሸከርካሪዎች እና ሌሎች ተያያዥ ንብረቶችን 10  

 

1,132,770,521.25

 

 

ድርድር

 

ልዩ

ድርድር

 

5

አለምገነት ንግድና ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር አዲስ አበባ ከተማ

አስተዳደር፣ ንፋስ

ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ

፣ ወረዳ 12

ግንባታዎች፤የመስሪያ ማሽኖች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ጥሬ እቃ እና ተረፈ- ምርቶች  

0.3967

 

213,818,338.64

 

ዝግ ጨረታ

 

 

ሁለተኛ

ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ ፤

 • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸዉን በመጥቀስ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ለሩቺ አግሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፣ ቢ.ኤች.ኦ ባዮ ፕሮዳክትስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ፣ ለይጋርሰሀዱታ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ኢቱር ቴክስታይል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡50 ሰዓት ድረስ እና ለአለምገነት ንግድና ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፤
 • ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
 • አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፤
 • 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
 • የኢቱር ቴክስታይል ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴ ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ በመጓጓዝ ወይም በክምችት ላይ ያሉ ግብዓቶች /ጥሬ ዕቃዎች/ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ያለቁ ምርቶችን በርክክብ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ /በዱቤ/ ከፍሎ መውሰድ አለበት፤
 • ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
 • በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፤
 • ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት I & II በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011–524-53-73/011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
 1. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ