የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢዛና የማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባልተከፈለ የመተማመኛ ሰነድ ክፍያ እዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱት የመለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Development-bank-of-Ethiopia-logo

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 09/15/2022
 • Phone Number : 0115245373
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/25/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢዛና የማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባልተከፈለ የመተማመኛ ሰነድ ክፍያ እዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱት የመለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተቁ የአስመጪ ስም የንብረት አድራሻ የንብረት ዝርዝር የጨረታ መነሻዋጋ (በብር) የጨረታ ሁኔታ የጨረታ ደረጃ ጨረታው የሚካሄድበት   ቀንና ሰዓት
1 ኢዛና የማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ አቃቂ ቃሊት ክ/ከተማ፣ ወረዳ 05 አስተዳደር ጀርባ ለወርቅ ማምረቻ ማሽን የሚውሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች 42,423,104.02 ዝግ ጨረታ አንደኛ ጥቀምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ፤

 • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸዉን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፤
 • ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
 • አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡በተጨማሪ አሸናፊው ባንኩ ላይ በዳግም ጨረታ ለሚደርስ ጉዳት ይጠየቃል፡፡
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፤
 • 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን ገዢው ይከፍላል፤
 • በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፤
 • ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት-I በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73 እና 011-524-41-21 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
 • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ