የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ማህበር ለ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለስፖርተኞች የምግብ አቅርቦት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ethiopian-insurance-corporation-Logo

Overview

 • Category : Catering Service
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0115159626
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/19/2022

Description

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ማህበር ለ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለስፖርተኞች የምግብ አቅርቦት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

 1. በዘርፉ የ2014 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፣
 2. የግብር መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርቲፊኬት ያለው፣
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መስቀል አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምሥራቅ አዲስ ዲስትሪክት ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05 ስፖርት ጽ/ቤቱ በመውሰድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ መጥተው ሰነዱን በመግዛት ሞልተው ሊያስገቡ ይችላሉ፡፡
 4. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ (Specification) በሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ­­15ኛው የሥራ ቀን ከሰኞ እስከ ዓርብ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ9፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በስፖርት ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000.00 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ በሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች አስፈላጊ ሕጋዊ ሰነዶች እና የሚጠየቁ ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ መግለጫን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ እና በአንድ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሸናፊው ተለይቶ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 8. ስፖርት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • የስፖርት ማህበሩ የሥራ ሰዓት ፡-

ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጥዋት    ከ2፡00-600             ከሰዓት በኃላ   ከ7፡00-10፡00    ዓርብ    ጥዋት         ከ2፡00-5፡30        ከሰዓት በኃላ   ከ7፡30-11፡00

ለበለጠ መረጃ በሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ክለብ

ስልክ ቁጥር ፡- 0115 15 96 26

አዲስ አበባ