የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሠማኮ/ የጨረታ ማስታወቂያ

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 01/16/2021
 • Phone Number : 0115155429
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/22/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሠማኮ/ ከዴንማርክ የቤተሰብ እቅድ /DFPA/ ከተባለ ለጋሽ ድርጅት ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተሠሩ የፕሮጀክት ሥራዎች ማስፈፀሚያ በሥራ ላይ የዋለ የገንዘብ እንቅስቃሴ የሂሳብ ምርመራ በታወቁ ኦዲተሮች በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-

 1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በሙያው የታደስ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
 4. በዋናው አዲተር መ/ቤት የተመዘገበና በመስኩ ሰርቲፋይድ የሆነበትን የሙያ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
 5. ሂሳቡን የሚመረምርበት ዋጋና የሂሳብ ምርመራው የሚጠናቀቅበት ጊዜ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል፣
 6. ተጫራቾች ከላይ በዝርዝር በተገለፀው መሰረት መሟላት የሚገባቸውን ሁሉ አሟልተው የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ ኢሠማኮ ግዥ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ቢሮ ቁጥር 216 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ6ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 6ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 8. የሂሰብ ሰነዶቹን ኢሠማኮ ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መመልከት ይቻላል፣
 9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

          የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን

            ስልክ ቁጥር፡ 0115-15 49 57/0115-15 54 29

 

Send me an email when this category has been updated