የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ያገለገሉ ቁም ሳጥኖች,መደርደሪያዎች,ልዩ ልዩ ወንበሮች,ጠረጴዛዎች ና የመሳሰሉትን አወዳድሮ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Office Items & Equipment sale
  • Posted Date : 06/01/2021
  • Phone Number : 0115573454
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/23/2021

Description

የአገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ያገለገሉ ቁም ሳጥኖች! መደርደሪያዎች! ልዩ ልዩ ወንበሮች!ጠረጴዛዎች!አግዳሚ ወንበሮች!ባለብረት ፋይል ካቢኔቶች! ኮምፒዩተሮች! ኘሪንተርና ፎቶኮፒ!የሽመና ዕቃና ተጓዳኝ ዕቃዎች ካስኮችና ተጓዳኝ ዕቃዎች የስፌት ክርዚኘ አጭርና ረጅም የወገብ ላስቲክ እቃዎችንና የመሳሰሉትን አወዳድሮ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተጠቀሰውን ንብረት ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት/ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር *ቦሌ መንገድ ቦሌ ማተሚያ ቤት ዝቅ ብሎ ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ፊትለፊት አልታ ኮምፒዩተር ያለበት ግራውንድ ከሚገኘው የኢትዩጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የሂሳብ ክፍል ዝርዝር መረጃውን የያዘውን የጨረታ ሰነድ ብር 50.00/ሀምሳ ብር በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው የማስታወቂያው ጊዜ ባለቀ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰአት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት በፌዴሬሽኑ ሂሳብ ክፍል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካያቸው በተገኙበት  ይከፈታል፡፡

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ህጋዊ በሆነ cpo ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አሸናፊ የሚሆነው አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ እቃውን በሰባት ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማንሳት አለበት፡፡
  • ዕቃውን ለማየት የምትፈልጉ ዕቃው በሚገኝበት ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ከአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ጎን በመኪና ማቆሚያው ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ግቢና ሌሎችም ንብረቱ በሚገኝባቸው የፌዴሬሽኑ የንብረት ማስቀመጫ ቦታዎች ጨረታው ተሸጦ እስከሚያልቅበት ቀን ድረስ ከጽ/ቤቱ የንብረት ክፍል ሰራተኛ ጋር በመሆንና በስልክ ደውላችሁ ግዜ በማመቻቸት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠመረጃ በ011 557 3454 ወይም በ011 558 2112 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

                   የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን

Send me an email when this category has been updated