የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በብሄራዊ ጽ/ቤቱ የሚገኘውን ቅጥር ግቢ እና በሌሎች የማህበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የ24 ሰአት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎት አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ የጥበቃ ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Red-Cross-Society-logo-3

Overview

 • Category : Security & Protection Equipment Guarding
 • Posted Date : 08/20/2022
 • Phone Number : 0115180175
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/05/2022

Description

የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በብሄራዊ ጽ/ቤቱ የሚገኘውን ቅጥር ግቢ እና በሌሎች የማህበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የ24 ሰአት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎት አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ የ1 (አንድ) አመት ውል በመፈራረም የጥበቃ ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

 1. በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት፣በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ነሐሴ 16 ቀን 2014ዓ/ም ጀምሮ የማይመለስ ብር100 (አንድ መቶ) በመክፈል አዲስ አበባ ስታዲየም አጠገብ ከሚገኘው የኢትዮጰያ ቀይ መስቀል ማህበር  ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 ዘወትር በስራ ሰዓት  በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ፣የቴክኒክ ሰነድ ኦርጅናል በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ በተለያዩ ኢንቨሎፖች በማድረግ አራቱንም ኢንቨሎፖች በአንድ ላይ በማሸግ  ከዚህ በታች በተጠቀሰው የማህበሩን አድራሻ “የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ጨረታ” የሚል በመጻፍ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች  የጨረታ ማስከበሪያ  ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ) በሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ  በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር  ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት በስራ ሰዓት ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 ለዚሁ ተግባር  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
 6. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115180175 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
 7. ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ብሔራዊ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር -0115180175

           ፖስታ ሣጥን ቁጥር-195

         አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ