የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ ለ1 (አንድ) ዓመት የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈራረም ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Red-Cross-Society-logo-6

Overview

 • Category : Transport Service
 • Posted Date : 12/31/2022
 • Phone Number : 0115180175
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/20/2023

Description

የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ ለ1 (አንድ) ዓመት የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈራረም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

 1. በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የጭነት አገልግሎት የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ሁለት ኢንቨሎፖች ፣የቴክኒክ ሰነድ ኦርጅናል በሌላ በአንድ ኤንቨሎፕ ፣ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በሌላ ኢንቨሎፕ እንዲሁም  አራቱንም ኢንቨሎፖች በአንድ ላይ በሌላ ትልቅ ኢንቨሎፐ በማሸግ  ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የማህበሩ አድራሻ እና ” የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ   ጨረታ” የሚል በመጻፍ የመጫረቻ ሰነዳቸውን  ጥር 10 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ወይም ቀደም ብሎ  ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች  የጨረታ ማስከበሪያ  ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ) በሲፒኦ ብቻ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር  ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ የአንድ ኩንታል በኪሎ ሜትር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው  ጥር 10 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት በስራ ሰዓት ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 ለዚሁ ተግባር  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
 6. ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ብሔራዊ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር –011 5 180175

ፖስታ ሣጥን ቁጥር-195

አዲስ አበባ፣

ኢትዮጵያ