የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮና የቤት እቃዎችን፣ደስኮቶኘ፣ላኘቶኝ፣ኮምፒውተሮችና ተዛማጅ እቃዎች ፎቶ ኮፒ ማሸን፣የተለያዩ ከብረት እና ቁርጥራጭ ብረቶችን፣ ያገለገሉ የእንጨት ፖሌቶችን፣ የተለየዩ መጠን ያላቸውን ድንኳኖችን፣ የስፌት ማሽን እና የመሳሰሉትን አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Red-Cross-Society-logo-4

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 01/25/2023
  • Phone Number : 0115150608
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 02/07/2023

Description

ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮና የቤት እቃዎችን፣ደስኮቶኘ፣ላኘቶኝ፣ኮምፒውተሮችና ተዛማጅ እቃዎች ፎቶ ኮፒ ማሸን፣የተለያዩ ከብረት እና  ከእንጨት ውጤት የተሰሩ ቁሳቁሶችን፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችን፣ ቁርጥራጭ ብረቶችን፣ ያገለገሉ የእንጨት ፖሌቶችን፣ የተለየዩ መጠን ያላቸውን ድንኳኖችን፣ የስፌት ማሽን እና የመሳሰሉትን አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 3ዐ/ዐ5/2ዐ15 ዓ.ም. ድረስ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ሳሊተምህረት ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከግዥ ዋና ክፍል በብር 1ዐዐ/ አንድ መቶ ብር / በመግዛትና እቃዎቹን     የቅ/ጽ/ቤቱ ማዕከላዊ መጋዘን በመጎብኘት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ 3ዐ/ዐ5/2ዐ15 ዓ.ም.  ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጅው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጨረታ የቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2 /ሁለት በመቶ/ በ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ Bank Guarantee አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው 3ዐ/ዐ5/2ዐ15 ዓ.ም.  በ8፡ዐዐ ሰዓት ተዘገቶ በእለቱ በ8፡3ዐ ሳሊተምህረት አካባቢ በሚገኘው የማኀበሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈለጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ሰልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር

አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር ዐ11 515 ዐ6 ዐ8

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 41ዐ76

አዲስ አበባ