የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ 6ኛው ዙር የቡና ቤተሰብ የሩጫ ማሊያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
- Posted Date : 08/26/2021
- Phone Number : 0115314125
- Source : Reporter
- Closing Date : 09/07/2021
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ 6ኛው ዙር የቡና ቤተሰብ የሩጫ ማሊያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- የሩጫ ማሊያው የክለቡን አርማ ቡኒ እና ቢጫ ይዘት የያዘ ሆኖ ደረጃውን በጠበቀ ፓሊስተር መሰራት አለበት፡፡
- የሩጫው ማሊያው የክለቡን እና የስፖንሰሮች ሎጐ ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 136 መግዛት ይችላሉ፡፡ ስለማሊያው ክብደትና ስለሚሰራበት ግብዓት እንዲሁም ዲዛይን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ እስከ ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክለቡ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ክለቡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ናሙና ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ 0115-31-41-25/0115-51-28-25
“ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ”