የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር የተሽከርካሪዎች እድሳት እና የጥገና ጋራዥ ለመምረጥ የወጣ የጨረታ

Family-Guidance-Association-of-Ethiopia-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Vehicle & Motorcycle Maintenance
 • Posted Date : 04/23/2021
 • Phone Number : 0114672300
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/13/2021

Description

በኢትዮጵያቤተሰብመምሪያማኀበር

የተሽከርካሪዎች እድሳት እና የጥገና ጋራዥ ለመምረጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር በትርፍ ላይ ያልተመሰረተ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት በ1958 ዓ.ም. የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ማኀበሩ በስምንት የአካባቢ ጽ/ቤቶች ሥር በስምንት ክልሎችና በሁለት የከተማ መስተዳድሮች በሚገኙ ከ50 በላይ የሚሆኑ የተዋልዶ ጤና ልዩ ክሊኒኮች፣ በወጣት ማዕከላት እና ኮንፊደንሻል የጤና አገልግሎት ክሊኒኮች የተዋልዶ ጤና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ማኀበሩ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ በርካታ ተሽከርካሪዎችን በማሠማራት የትራንስፖርት አገልግሎትን የተሳካ እንዲሆን ጥረት ያደርጋል፡፡ የተሳፋሪዎችን እና የተሽከርካሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም የተሽከርካሪዎችን የአገልግሎት ዘመን ለማራዘም ማኀበሩ ያሉትን ተሽከርካሪዎች ብቃት ባለው ጋራዥ በቂ ጥገናና እድሳት እንዲደረግላቸው ያደርጋል፡፡  በመሆኑም ማህበሩ በስሩ ላሉት ከ70 በላይ ተሽከርካሪዎች ጥገናና እድሳት የሚያደርጉ ጋራዦችን አወዳድሮ መምረጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የተሽከርካሪ ጥገናእና እድሳት አገልግሎት መስጠት የምትፈልጉ ደረጃ አራት የቀላል ተሽከርካሪ ሁለገብ ጥገና ጋራዦች እና ደረጃ አምስት የቀላል ተሽከርካሪ ሁለገብ ጥገና ጋራዦች ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ሠነድ በማይመለስ ብር 5ዐ.ዐዐ በመግዛት በጨረታው እንደትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

ተጫራቾች

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው
 2. ጋራዡ በቂ የስራ ቦታ፤ ወርክሾፖች፤ ማሽኖች እና የሰው ሀይል እንሁም የታደሰና ሁለገብ የኢንሸራስ ሽፋን ያለው
 3. ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን ሠነድ የማኀበሩ ዋና መሰሪያ ቤት በመቅረብ በመግዛት እና የጥገና የእድሳት ሥራ እና የመለዋወጫ ዋጋ ያልተጣራ ትርፍ በፐርሰንቴጅ (በ%) ዋጋ በመስጠት መጫረት የሚችል
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቁያው በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ከወጣበት ከሚያዚያ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ዋናው መ/ቤት ማስገባት ይችላሉ፡፡የንግድ ፈቃዳቸውን እና ሌሎች ተያያዥ ሠነዶችንም ማቅረብ አለባቸው
 5. ጨረታው ሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡3ዐ ስዓት ይከፈታል፡፡
 6. ማህበሩ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የስድስት ወር ወይም የአመት ውል በመግባትና የሚያገኘውን አገልግሎት ብቃት በመገምገም ውሉን እስከ ሶስት ዓመት ድረስ ሊያራዝም ይችላል፡፡
 7. ማኀበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው፡፡
 8. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
 9. ለጨረታ የቀረበው ዋጋ ቫትንም ጨምሮ መሆን አለበት
 10. ማህበሩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

ፖ.ሳ.ቁጥር 5716

ስልክ ቁጥር ዐ1146723ዐዐ

ሪቸ መስከረም ማዞሪያ 2ዐዐ ሜትር ገባብሎ