የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች አገልግሎቱን ለማዳረስ እየተገለገለባቸው ያሉ በርካታ ቀላልና እና መካከለኛ የመስክ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም እድሳት እና የጥገና አገልግሎቱን መስራት ለሚችሉ ህጋዊ እና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪ ጋራዦች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Family-Guidance-Association-of-Ethiopia-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Garage Service
 • Posted Date : 12/24/2022
 • Phone Number : 011467200
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/11/2023

Description

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

የተሽከርካሪ እድሳትና ጥገና አገልግሎት ሰጪ ጋራዦችን አወዳድሮ ለማሰራት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ለትርፍ ያልተቋቋመ እና የተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በ1958 ዓ.ም. የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ የስነተዋልዶ ጤና ህክምና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው፡፡ ማኅበሩ የስነተዋልዶ ጤና በተለይ የወጣቶች የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች በሚገኙት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቹ እና አገልግሎት መስጫ ክሊኒኮቹ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች አገልግሎቱን ለማዳረስ እየተገለገለባቸው ያሉ በርካታ ቀላልና እና መካከለኛ የመስክ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም አውቶብሶችን መደበኛ ሰርቪስ  እና በብልሽት ወቅት ለሚያስፈልግ የጥገና አገልግሎት ውል በመግባት የተሽከራካሪዎቹን መደበኛ ስርቪስ፤ እንዲሁም  እድሳት እና የጥገና አገልግሎቱን መስራት ለሚችሉ ህጋዊ እና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪ ጋራዦች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተገለፀው መሰረት የማህበሩን በርካታ የመስክ እና ቀላል ተሽከርካዎችን እንዲሁም አውቶብሶችን በተወሰነ ጊዜ የታሰረ ውል በመግባት የመኪኖቹን መደበኛ ሰርቪስ እና ጥገናዎችን ለማከናወን የምትፈልጉና በቂ የስራ ልምድ፤ ወርክሾች፤ ማሽኖችና የሰለጠነ የሰው ሀይል ያላችሁ መስፈርቱን የምታሟሉ ደረጃ 4 እና 5 የቀላል ተሽከርካሪ ሁለገብ የጥገና ጋራዦችን ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ሠነድ በማይመለስ ብር 10ዐ.ዐዐ በመግዛት በጨረታው እንደትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ተጫራቾች

 1. የደረጃ 4 እና የደረጃ 5 የቀላል ተሽከርካሪ ሁለገብ ጥገና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
 2. በቂ የስራ ቦታ፤ ወርክሾች የስራ ማሽኖች እና የሰለጠነ የሰው ሀይል እንዲሁም የታደሰ ሁለገብ የኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸው ተጫራቾች ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሠነድ የማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ በመግዛት የሚችሉ፤
 3. ተጫራቾች የፋይናንስ ፕሮፖዛላቸውን ለብቻ፤ የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን ለብቻ በተገቢው መሰረት ሞልተው ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት እንደዚሁም ብር 10000 የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ለብቻው ካሸጉ በኋላ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ ከተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ከወጣበት ከ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ዋናው መ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፤
 4. ጨረታው ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱና በሰአቱ ለመገኘት በፈቀዱና በተገኙ ተጫራቶች ወይም በሰአቱ በተገኙ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ከቀኑ በ8፡0ዐ ሰዓት ይከፈታል ፡፡
 5. ማኀበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው፡፡
 6. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

አድራሻ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

ፖ.ሳ.ቁጥር 5716፤ ስልክ ቁጥር ዐ1146723ዐዐ

ሪቼ መስከረም ማዞሪያ 2ዐዐ ሜትር ገባ ብሎ