የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የማህበሩ ክበብ ውስጥ በይዘቱ የተሟላና ጥራት ያለው የክበብ (የምግብ፣ የትኩስና የለስላሳ መጠጦች) አገልግሎት መስጠት ለሚችሉ ህጋዊ እና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አወዳድሮ የክበቡን አገልግሎት መስጠት ይፈልጋል፡፡

Family-Guidance-Association-of-Ethiopia-logo-reportertenders-2

Overview

 • Category : Catering Service
 • Posted Date : 09/18/2021
 • Phone Number : 0114672300
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/04/2021

Description

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

ለሰራተኞቹ፣ ለክሊኒክ ተጠቃሚዎች፤ እና ለስልጠና ተሳታፊዎች የተሟላ የክበብ (የካፌ) አገልግሎት ማቅረብ የሚችሉ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ለማወዳደር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ለትርፍ ያልተቋቋመ እና የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በ1958 ዓ.ም. የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ የስነተዋልዶ ጤና ህክምና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው፡፡ ሪቼ (መሷለኪያ) አካባቢ የሚገኘው የማኅበሩ ዋናው መ/ቤት፤ 24 ሰአት አገልግሎት የሚሰጥ የእናቶችና ህፃናት ህክምና እና የስልጠና ማእከሉ በጋራ የሚገኙበት ህንፃ በእናቶችና ህፃናት ለይ ያተኮረ ዘርፈ ብዙ የተዋልዶ ጤና ህክምና እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር በዋናው መ/ቤት ለሚገኙ በርካታ ሰራተኞቹ፤ ለህክምና ወደ ማእከሉ ለሚመጡ ተገልጋዮቹ እና በስልጠና ማዕከሉ ስልጠና ለሚወስዱ የስልጠና ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች በዋናው መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማህበሩ ክበብ ውስጥ በይዘቱ የተሟላና ጥራት ያለው የክበብ (የምግብ፣ የትኩስና የለስላሳ መጠጦች) አገልግሎት መስጠት ለሚችሉ ህጋዊ እና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አወዳድሮ የክበቡን አገልግሎት መስጠት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተገለፀው መሰረት በማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ክበብ ውስጥ ከነፃ የቤት የውሃና የመብራት አቅርቦት ጋር የተሟላ የክበብ (የካፍቴሪያ) ገልግሎት ማቅረብ የምትፈልጉና መስፈርቱን የምታሟሉ አገልግሎት ሰጪዎች ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ሠነድ በማይመለስ ብር 10ዐ.ዐዐ በመግዛት በጨረታው እንደትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

ተጫራቾች

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
 2. ቫት የተመዘገቡና የቫት ሰርተፍኬትና የታክስ ክሊራንስ ሰርፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
 3. ተጫራቾች ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሠነድ የማኀበሩ ዋና መሰሪያ ቤት በመቅረብ በመግዛት የሚችሉ
 4. ተጫራቾች የፋይናንስና የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን በተገቢው መሰረት ሞልተው ለእያንዳነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት እንደዚሁም ብር 5000 የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ለብቻው ካሸጉ ቡሃላ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ ከተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቁያው በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ከወጣበት ከመስከረም 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ዋናው መ/ቤት ማስገባት ይችላሉ፤
 5. ጨረታው ሰኞ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱና በሰአቱ ለመገኘት በፈቀዱና በተገኙ ተጫራቶች ወይም በሰአቱ በተገኙ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት በእለቱ ከሰአት ቡሃላ በ8፡0ዐ ስዓት ይከፈታል፡፡
 6. ማኀበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው፡፡
 7. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

አድራሻ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

ፖ.ሳ.ቁጥር 5716

ስልክ ቁጥር ዐ1146723ዐዐ

ሪቼ መስከረም ማዞሪያ 2ዐዐ ሜትር ገባ ብሎ