የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስቲል) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 32,650 ኪሎ ግራም (ሳላሳ ሁለት ሺ ስድስት መቶ አምሳ ኪ/ግ) አልሙኒየም ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 2,000 ኪሎ ግራም (ሁለት ሺ ኪ/ግ)፤ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

NATIONAL-BANK-OF-ETHIOPIA-logo-1

Overview

 • Category : Steels & Aluminium supply & sale
 • Posted Date : 09/13/2022
 • Phone Number : 0115175293
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/03/2022

Description

NATIONAL BANK OF ETHIOPIA

የጨረታ ማስታወቂያ

ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ዓይነት ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር ኢብባ/ኢንትአአዳ/ስቲል/አልሙኔም/01/2015

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስቲል) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 32,650 ኪሎ ግራም (ሳላሳ ሁለት ሺ ስድስት መቶ አምሳ ኪ/ግ) አልሙኒየም ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 2,000 ኪሎ ግራም (ሁለት ሺ ኪ/ግ)፤ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የቀበሌ መታወቂያ፤ የታደሰ ፓሰፖርት፤ የታደሰ መንጃ ፍቃድ ወይም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕንጻ 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቢሮ አንደኛ ፎቅ በመምጣት ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶችን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣፡
 3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ከገዙበት እና ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም23፤2015 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እከ 5፡30 እንዲሁም ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት መመልከት ይችላሉ፣፡
 4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት ማለትም ለስቲል ብር 50,000.00 (አምሳ ሺ ብር)እና  ለአልሙኒየም ብር10,000.00 (አስር ሺብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕንጻ-2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. አንድ ተጫራች ለጨረታ ግምገማ ብቁ የሚሆነው መስፈርቱ የዋጋ ማቅረብያ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በሰነዱ የተመለከቱትን አሟልቶ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡
 6. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው እንዲወጣ/እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡
 7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ24ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕንጻ-2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው ሁለተኛ ፎቅ ቪድዮ ኮንፈረንስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ባሉት 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና፤ በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የእያንዳንዱ ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት ዓይነት ግምታዊ ጠቅላላ መጠን ተወስዶ ባሸነፉበት የ1ኪሎ ግራም ዋጋ መሰረት ተሰልቶ ጠቅላላ ዋጋ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሂሳብ ስም በባንክ ትራንስፈር መክፈል አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶቹ ግምታዊ መጠን በርክክብ ወቅት በሚዛን ፕሪንት አውቱ ንባብ እና የሚዛን ደረሰኝ ከሚገኘው ትክክለኛ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውሉ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት በልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን ከባንኩ ተመላሽ ሊደረግለት የሚገባ ገንዘብ ካለም በትክክለኛው የገንዘብ መጠን ልክ ባንኩ በኤሌክትሮኒክ ባንክ ትራንስፈር ወደ ድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ተመላሽ ያደርጋል ፡፡
 9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት በራሳቸው ወጪ የማስጫን፤ የማጓጓዝ፤የሚዛን፤ የጉልበት ሰራተኞች እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች በመሸፈን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶቹ ከሚገኝበት ሥፍራ ቅርብ በሆነ በመንግስት ተቋም በባለቤትነት የሚተዳደር የምድር ሚዛን ህጋዊ ደረሰኝ እና ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል እና የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ከሚመለከተው አካል የተሰጠው መሆኑን ተረጋግጦ አሸናፊው ተጫራች ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ  ብረታ ብረቶቹ በማስመዘን ውል በፈረመው በ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ ሙሉ በሙሉ በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
 10. ባንኩ ባወጣው በዚህ ጨረታ ላይ የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ ተወዳደረ ሆኖ የቀረበ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
 11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-5175293 ወይም 0115175027 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
 12. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል እና በማናቸውም ሁኔታ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

አዲስ አበባ

ማሳሰቢያ፡- በዚህ የጨረታ ሰነድ “ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት” የሚለው ስያሜ ለጨረታ የቀረቡትን ሁለት የብረታ ብረት ዓይነቶች ማለትም ለባንኩ አገልግሎት የማይሰጡ ስቲል እና አልሙኒየም የሚያመለክት ነው፡፡