የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን በ2014 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 26 ቀን 2014 እስከ ጥር 30/2014 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው ኤግዚቢሽንና ባዛር አገልግሎት የሚውሉ ኤግዚቢሽን ማሳያ ቦታ መከራየት ይፈልጋል፡፡

Federal-Corporate-Agency-Logo-4

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 12/29/2021
 • Phone Number : 0115573436
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/07/2022

Description

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን በ2014 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 26 ቀን 2014 እስከ ጥር 30/2014 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው ኤግዚቢሽንና ባዛር  አገልግሎት የሚውሉ ኤግዚቢሽን ማሳያ ቦታ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-

 1. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የዘመኑ የተደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች መ/ቤት የተሰጠ ክሪላንስ ወይንም የድጋፍ ደብዳቤ እና በግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ሰነድ ሀርድ ኮፒ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50(ሀምሳ) በመክፈል ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ ወረድ ብሎ ሸዋ ዳቦ መጋገሪያ ህንጻ ላይ በሚገኘው መ/ቤታችን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 34 ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. በሚወዳደሩት የኢግዚቢሽን ማሳያ ቦታ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪ እና አንቡላንስ በጊቢው እንዲኖር ማድረግ የሚችል እና የጊቢውን ደህንነት በቂ ልምድ እና ችሎታ ባላቸው የጥበቃ አባላት ቁጥጥር ማድረግ የሚችል የሰው ኃይል ያለው፡፡
 4. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 5. ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአንድ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ በሚቆጠር 10(አስር) ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 7. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 8. በተጠየቀው ቁጥርና ዓይነት መሠረት ውጭ በከፊል ማቅረብ አይቻልም፡፡
 9. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ላይ ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድቦንድ) ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% እና ከዚያ በላይ በማስላት በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ ደረሰኙን በመወዳደሪያ ሰነዱ ላይ ለብቻው በፖስታ በማሸግ አያይዘው መቅረብ አለበት፡፡
 11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሞከረ እንደሆነ ከጨረታው የሚሰረዝ እና ለወደፊቱም በመንግስት ግዢ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደረግ ሲሆን ያስያዘውም የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
 12. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ከተገለጸ በኃላ በ5 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ ካልፈረሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
 13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ሜክሲኮ ከኬኬር ህንጻ ወረድ ብሎ ሸዋ ዳቦ መጋገሪያ ህንጻ

2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 34  የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 0115573436

የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን

አዲስ አበባ